በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፌዴራሉ ዳኛ በትራምፕ ተባባሪ ጠበቆች ላይ ማዕቀብ ጣሉ


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድስቴትስ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድስቴትስ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድስቴትስ ፌዴራሉ ፍርድ ቤት ዳኛ፣ ከቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ጋር፣ ግንኙነት አላቸው በተባሉ ዘጠኝ ጠበቆች ላይ የገንዘብ ቅጣቶችና ሌሎች ማዕቀቦችን ጥለውባቸዋል፡፡

ዳኛው ውሳኔውን ያሳለፉት በሚችጋን ክፍለ ግዛት የ2020 የምርጫ ውጤቶችን አስመልከቶ በቀረበው የተቃውሞ ክስ ላይ ፍርድ ቤቱን በማሳሳታቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

“በፍርድ አሰጣጥ ላይ የተፈጸመ ታሪካዊና የከፋ በደል ነው” ያሉት የፌደራል ፍርድ ቤቱ ዳኛ ሊንዳ ፓርከር፣ ውሳኔቸውንአስመልከተው በጻፉት ላይ “በተጭበረበረ ምርጫ የተጣሱ መብቶችን ማስከበር አንድ ነገር ነው፡፡ ምንም የተጣሰ ህግ ወይም መብት ሳይኖር የፌድራሉን ፍርድቤትና የአሜሪካን ህዝብ ማታለል ደግሞ ሌላ ነገር ነው” ብለዋል፡፡

በውሳኔያቸውም 9ኙም የህግ ባለሙያዎች የ12 ሰዓታት ትምህርት እንዲወስዱ የሚችጋን ባለሥልጣናት ክሱን ለመከላከል ያወጡትን ወጭ እንዲሸፍኑ ማዘዛቸው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG