ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ የወረዳ ወይም ዲስትሪክት ዳኛ፣ የዩናይትድ ስቴትስና ሜክሲኮ ድንበርን፣ አሳብረው ሲገቡ የተያዙ፣ ስደተኛ ቤተሰቦችን፣ ወደ አገራቸው እንዲባረሩ የሚያዘውን የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ትዕዛዝ ውድቅ አደረጉ፡፡
በትናንትናው እለት ውሳኔውን የሰጡት ዳኛ ኢሜትሱሊቫን፣ የትራምፕ አስተዳደርን ትዕዛዝ የሚሽረው ውሳኔ በ14 ቀናት ውስጥ ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ባይደን፣ ካንዳንዶቹ የስደተኞች መብት ተሟጋቾች፣ ከጤና ባለሙያዎችና ከዴሞክራት ባልደረቦቻቸው፣ በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩስደተኞች፣ የፖለቲካ ጥገኝነት የሚከለክለውና ታይትል 42 በመባል የሚታወቀውን፣ የቀድሞው አስተዳደር ትዕዛዝ እንዲያስቀሩ፣ ከፍተኛ ጫና እየተደረገባቸው መሆኑንም ተመልክቷል፡፡