በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአሜሪካ ሥራ አጥነት አሽቆልቁሏል


ፎቶ ፋይል፦ የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ ሲቪኤስ ፋርማሲ፤ ሳንፍራንሲስኮ፣ ካሊፎርኒያ
ፎቶ ፋይል፦ የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ ሲቪኤስ ፋርማሲ፤ ሳንፍራንሲስኮ፣ ካሊፎርኒያ

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ባለፈው ወር ብቻ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰው መቀጠሩንና የሥራ አጥነት መጠኑም በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉን የሃገሪቱ የሥራና ስታትስቲክስ ቢሮ ዛሬ አስታውቋል።

የዋጋ ግሽበትና የኢኮኖሚ ድቀት ሥጋት እያለም ባለፈው ወር 528 ሺህ ሰው የተቀጠረ ሲሆን የሥራ አጥነት መጠኑም ወደ 3.5 በመቶ መውረዱ ተገልጿል።

አጠቃላይ የሃገር ውስጥ ምርቱ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ሩብ ዓመታት በተክታታይ ቢወርድም በብዙ የምጣኔ ኃብት ባለሙያዎች ዘንድ የሥራ ዕድሉ መስፋት ኢኮኖሚው የከፋ ድቀት ውስጥ እንዳይገባ ታድጓል የሚል እምነት እንዳለ እየተነገረ ነው።

ባለፈው ወር ይፈጠራል ብለው ኢኮኖሚስቶች የገመቱት አዲስ የሥራ ዕድል 250 ሺህ ነበር።

XS
SM
MD
LG