በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ በጃፓን ያካሄዱትን የአራት ቀናት ጉብኝት አጠናቀቁ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በጃፓን ያካሄዱትን የአራት ቀናት ጉብኝት ሲያጠናቅቁ ቻይና እየመጠቀች በሄደችበት በአሁኑ ወቅት በዩናይትድ ስቴትስና በጃፓን መካከል ወታደራዊ ትብብር የማጠናከሩ ጉዳይ ትኩረት ተደርጎበታል።

የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ዛሬ ማለዳ ፕሬዚዳንት ትረምፕን 'JS Kaga' በተባለው ሄሊኮፕተር ሊበርበት በሚችል የጦር መርከብ ላይ አስተናግደዋል። ይኸው የጦር መርከብ በቅርቡ በአሜሪካ የተሰራውን F-35ን አይነት ሱበርሶኒክ ስቲልት ጄት ተዋጊ አውሮፕላን እንዲበርበት ተድርጎ ይሰራል።

ሁለቱ መሪዎች ባደረግዋቸው ንግግሮች ቻይናን በስም ባይጠቅሱም ቻይና ፓሲፊክ ላይ ያላት ጠንካራ ወታደራዊ ህልውና እንዳሳሰባቸው ግልፅ ነው ታብሏል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG