በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ኮሪያና በጃፓን መካከል ያለው የንግድ ውዝግብ


በደቡብ ኮሪያና በጃፓን መካከል ያለው የንግድ ውዝግብ እየተጧጧፈ በመጣበት በአሁኑ ወቅት፣ ዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛውን የሽምግልና ሚና ልትጫወት መሆኗ ተነገረ።

በዚህ ሳምንት መግቢያ ላይ ጃፓንን የጎበኙት የምሥራቅ እስያ ከፍተኛ የዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማት፣ ሲኦል ውስጥ በዛሬው ዕለት ከደቡብ ኮሪያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ተገናኝተው፣ ውዝግቡ በቶሎ ሊፈታ እንዲገባው ማሳሰባቸው ተሰምቷል።

የምሥራቅ እስያና ፓሲፊክ ጉዳዮች ረዳት ዉጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዴቪድ ስቲልዌል እንደገለፁት፣ የሁለቱም ወዳጅ የሆነችው ዩናይትድ ስቴትስ፣ ሁለቱም ሀገሮች ውዝግቡን ለመፍታት የጀመሩትን ጥረት በምትችለው ሁሉ ትረዳለች።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG