በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ ኮሪያ፣ አሜሪካ እና ጃፓን የባህር ኃይል ልምምድ አደረጉ


ደቡብ ኮሪያ፣ አሜሪካ እና ጃፓን የባህር ኃይል ልምምድ አደረጉ
ደቡብ ኮሪያ፣ አሜሪካ እና ጃፓን የባህር ኃይል ልምምድ አደረጉ

ደቡብ ኮሪያ፣ አሜሪካ እና ጃፓን በዛሬው ዕለት የሶስትዮሽ የሚሳዬል መከላከያ ልምምድ ከደቡብ ኮሪያ በስተ መሥራቅ በሚገኝ ዓለም አቀፍ የውሃ አካል ላይ አድርገዋል።

ኢጀስ የተባለውን የመከላከያ ቴክኖሎጂ የታጠቁ የደቡብ ኮርያ፣ የአሜሪካና የጃፓን የባህር ኃይል መርከቦች ምሥራቅ ባህር ወይም በጃፓኖቹ ዘንድ ‘የጃፓን ባህር’ ተብሎ በሚጠራው የውሃ አካል ላይ ልምምዱን አድርገዋል።

ሦስቱም አገሮች ባወጡት መግለጫ የባህር ላይ ልምምዱ የደህንነት ትብብራቸውንና የመልሶ ማጥቃት ሥርዓታቸውን ለማጠናከር እንደሚጠቅም አስታውቀዋል።

የሦስቱ አገራት ልምምድ የመጣው ሰሜን ኮሪያ፣ በደቡብ ኮሪያና አሜሪካ ለተደረገው ልምምድ መልስ ከባድ መሣሪያዎችንና ሚሳዬሎችን በተኮሰች ከሣምንት ባነሰ ግዜ መሆኑ ነው።

XS
SM
MD
LG