በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቻይና በኮሮናቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 132 ደረሰ


ቻይና ውስጥ በኮሮናቫይረስ በሽታ የሞቱት ሰዎች ብዛት 132 በደረሰበት በአሁኑ ወቅት ዛሬ ለመጀመጀሪያ ጊዜ የውጭ ሀገራት ተወላጆች ከሀገሪቱ ወጥተዋል።

ወደ ቻይና የሚደረገውን ጉዞ አጠንክረው የሚያግዱት ሀገሮችም ተበራክተዋል። አንድ የጄት አይሮፕላን 206 የጃፓን ተወላጆችን ከቻይናዋ ከተማ ውሃን ወደ ጃፓን ቶክዮ ሀኔዳ አውሮፕላን ማረፍያ አድርሰዋል። ከመንገደኞቹ አራቱ አሞናል በማለታቸው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። መንገደኞቹ ከቻይና ከመነሳቸው በፊትና ጃፓን ከደረሱ በኋላ ለመመርመር ሲባል የህክምና ሰራተኞች አውሮፕላኑ ውስጥ እንደነበሩ ተገልጿል።

አሶሼትድ ፕሬስ የዜና አገልግሎት በዘገበው መሰረት ማንነታቸው ያልተገለጸ አሜሪካውያን ከውሀን ከተማ ወደ አንኮሬጅ አላስካ በጄት አውሮፕላን ተወስደዋል፤ ሲገቡ ይመረመራሉ።

አውስትራልያ፣ ኒው ዚላንድ፣ ፈረንሳይ፣ ሩስያና ሌሎች ሃገሮችም ዜጎቻቸውን በያዝነው ሳምንት ከውሃን ከተማ የማስወጣት እቅድ እንዳላቸው አስታውቀዋል።

ቻይና ውስጥ በኮሮናቫይረስ የታመሙ ሰዎች ብዛት ከ 5,900 በላይ መድረሱን የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ባለሥልጣኖች ገልጸዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG