በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአሜሪካ ተማሪዎች ፍልስጤማውያንን በመደገፍ የሚያደርጉት አድማ እንደቀጠለ ነው


በካልፎርኒያ ዩኒቨርስቲ የሎስ አንጀለስ ግቢ የፍልስጤማውያን ደጋፊዎች በአንድ ወገን እና የእስራኤል ደጋፊዎች በሌላ ሆነው ተጋጭተዋል፣ ፖሊስ መሃል ገብቶ ለያይቷቸዋል፤ እአአ ግንቦት 1/2024
በካልፎርኒያ ዩኒቨርስቲ የሎስ አንጀለስ ግቢ የፍልስጤማውያን ደጋፊዎች በአንድ ወገን እና የእስራኤል ደጋፊዎች በሌላ ሆነው ተጋጭተዋል፣ ፖሊስ መሃል ገብቶ ለያይቷቸዋል፤ እአአ ግንቦት 1/2024

በአሜሪካ በሚገኙ በርካታ ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆች ፍልስጤማውያንን በመደገፍ የሚደረገው የተማሪዎች የተቃውሞ አድማ ቀጥሏል።

በካልፎርኒያ ዩኒቨርስቲ የሎስ አንጀለስ ግቢ ዛሬ ረቡዕ ማለዳ የፍልስጤማውያን ደጋፊዎች በአንድ ወገን እና የእስራኤል ደጋፊዎች በሌላ ሆነው ተጋጭተዋል።

ተማሪዎቹ በቡጢ፣ በካልቾና በቆመጥ ጭምር ድብድብ ላይ ሳሉ ፖሊስ መሃል ገብቶ ለያይቷቸዋል።

በመላው አሜሪካ ከኒው ዮርክ እስከ ቴክሳስና ካልፎርኒያ በተዛመተው ተቃውሞ፣ ተማሪዎች ድንኳን ሠርተው በመቀመጥ ዩኒቨርስቲዎቻቸው ከእስራኤል ጋራ ወይንም በጋዛ የሚካሄደውን ጦርነት ከሚደግፉ ወገኖች ጋራ ምንም ዓይነት ሥራ እንዳያከናውኑ በመጠየቅ ላይ ናቸው።

ኒው ዮርክ በሚገኘው ከሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የነበረውን በድንኳን የመቀመጥ አድማ ፖሊስ መበተኑ ታውቋል። የፍልስጤማውያን ደጋፊዎች ያገቱትን ሕንጻም አስለቅቋል።

የኒው ዮርኩ ከንቲባ ኤሪክ ኤደምስ ወደ 300 የሚጠጉ ሰዎች በከሎምቢያ እና ሲቴ ኮሌጅ መያዛቸውን አስታውቀዋል።

ከቬትናም ጦርነት ወዲህ የታየ ትልቁ የተማሪዎች ንቅናቄ እንደሆነ በሚነገረው ተቃውሞ፣ በመላ ሃገሪቱ እስከ አሁን ከ1ሺሕ በላይ ሰዎች በሕግ አስከባሪዎች መያዛቸው ታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG