በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኔታንያሁ የአሜሪካ ጉብኝታቸውን አቋርጠው ተመለሱ


የእሥራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔተናሁ ፣ ጋዛ ሰርጥ ላይ በደረሰው የሮኬት ጥቃት ምክንያት የዩናይትድ ስቴትስ ጉብኝታቸውን አቋርጠው ዛሬ ወዳገራቸው ተመለሱ። ድንገተኛ ቢሆንም ግን፣ ኔተናሁ ወዳገራቸው ከመመለሳቸው አስቀድሞ ከዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ጋር ተገናኘው መወያየታቸው ታውቋል።

የእሥራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ነገ ማክሰኞ ማታ ዋይት ኃውስ እራት ሊበሉ ቀጠሮ እንደነበራቸውና፣ ለእሥራኤል ድጋፍ ከሚያሰባስበው በአሜሪካ-እሥራኤል ሕዝባዊ ጉዳዮች ኮሚቴ ላይ ቀርበው ንግግር ለማድረግም ዕቅድ እንደነበራቸው ታውቋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ጉብኝታቸውን መቋረጥ አስመልክተው በሰጡት ቃል፤ እሥራኤል ላይ ለደረሰው የጭካኔ ጥቃት ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስዱ ቃል ገብተዋል።

ሀማስ በሚጠረጠርበት በዚህ ማዕከላዊ እሥራኤል ሰሜናዌ-ምሥራቅ ቴል-አቪቭ ውስጥ በሚገኝ መኖሪያ ቤት ላይ በደረሰው የሮኬት ጥቃት፣ ሰባት ሰዎች መቁሰላቸው የተለጸ ሲሆን፣ የእሥራኤል ጦር ኃይል በበኩሉ፣ ጋዛ ሰርጥ ውስጥ በሚገኙ የሀማስ ይዞታዎች ላይ የአጻፋ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG