ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ጋዛን አልምተው "የመካከለኛው ምሥራቅ ሪቪየራ (የባሕር ዳር መዝናኛ)" ሲሉ ወደጠሩት ለመቀየር ላላቸው ሃሳብ ወታደሮችን የመላክ ዕቅድ እንደሌላቸው ኋይት ሐውስ ትላንት ረቡዕ አስታውቋል፡፡ ፍልጤማዊያኑ ወደ ሌላ ሀገር ሄደው አንዲሰፍሩ የሚደረገውም በጊዜያዊነት እንደሆነ ገልጿል፡፡
ይሕ ለውጥ የተደረገው ታዲያ ዕቅዱ በዓለም ዙሪያ ተቃውሞ ካስከተለ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም "ምንም ዓይነት የጎሣ ማጽዳት አድራጎት" እንዳይፈጸም ካስጠነቀቀ በኋላ ነው፡፡
የአሜሪካ ድምጽ የኋይት ሐውስ ዋና ዘጋቢ ፓትሲ ዊዳኩስዋራ ያጠናቀረችው ዘገባ ነው።
መድረክ / ፎረም