በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ለእስራኤል ሊላክ የነበረን መሣሪያ አዘገየች


ፎቶ ፋይል፦ የአሜሪካ እና የእስራኤል ባንዲራዎች ታይተዋል።
ፎቶ ፋይል፦ የአሜሪካ እና የእስራኤል ባንዲራዎች ታይተዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን አስተዳደር ቦይንግ ሠር የሆኑና ለእስራኤል ሊላኩ የነበሩ መሣሪያዎችን እንዲዘገይ አድርጓል ሲሉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አራት ምንጮች ለሮይተርስ ዜና ወኪል ተናግረዋል።

ለአሜሪካ የቅርብ አጋር ለሆነችው እስራኤል የተላለፈ ግልጽ የፖለቲካ መልዕክት እንደሆነ ከምንጮቹ አንዱ ጠቁመዋል።

መሣሪያዎቹ እንዲዘገዩ የተደረገው እስራኤል በራፋ ላይ ያቀደችውን የምድር ጥቃት፣ ሲቪሎች የማይጎዱበት ሁኔታ እስኪፈጠር እንድታዘገይ ዋሽንግተን በይፋ ግፊት በማድረግ ላይ ባለችበት ወቅት ነው።

የእስራኤል መከላከያ፤ ወታደሮቹ ወደ ራፋ መሻገሪያ ሲዘልቁ የሚያሳይ ቪዲዮ የለቀቀ ሲሆን፣ ወሳኝ በሆነው መሻገሪያ ቁጥጥር ለማድረግ እንዲያስችለው መሆኑን አስታውቋል።

የእስራኤል እርምጃ የመጣው፣ ሐማስን ሙሉ ለሙሉ ለመደምሰስ በራፋ ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ወሳኝ እንደሆነ ለሳምንታት ስታስታውቅ መክረሟን ተከትሎ ሲሆን፣ አሜሪካ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ሌሎችም ሃገራት፤ ፍልስጤማውያን በብዛት ተሰብስበው በሚኖሩበት ቦታ ጥቃት መሰንዘር፣ ሰብዓዊ ቀውስ ይፈጥራል ሲሉ በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው፡፡

የአሜሪካው ብሔራዊ የፀጥታ ም/ቤት ቃል አቀባይ ጃን ከርቢ፤ የእስራኤሉ የራፋ ዘመቻ በመጠኑ ውስን እንደሆነ የሃገሪቱ ባልስልጣናት እንዳመለከቱ ሲናገሩ፤ የእስራኤሉ የመከላከያ ሚኒስትር ዮአዝ ጋላንት በበኩላቸው፣ በካይሮ በመካሄድ ላይ ያለው ድርድር በሐማስ የታገቱትን የማስለቀቅ ውጤት የማያመጣ ከሆነ፣ በራፋ ላይ ሰፋ ያለ ዘመቻ እንደሚካሄድ አስጠንቅቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG