በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጄነራል ቃሲም ሱሌይማኒ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ከ40 በላይ ሰዎች ህይወት አለፈ


በዩናይትድ ስቴትስ የድሮን ጥቃት በተገደሉት የኢራኑ ወታደራዊ አዛዥ ቃሲም ሱሌይማኒ ዛሬ ማክሰኞ በተከናወነው የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ቢያንስ አርባ የሚሆኑ ሰዎች ተረጋግጠው መሞታቸውን እና ሌሎች ከሁለት መቶ በላይ መጎዳታቸውን የኢራን መንግሥት የዜና ማሰራጫዎች ዘግበዋል።

በጄነራሉ የትውልድ ከተማ ኬርማን ውስጥ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ከመፈጸሙ በፊት አክብሮታቸውን ለመግለጽ በብዙ አስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገኝተው እንደነበር ታውቋል። ቀደም ብሎ ተመሳሳይ ሥነ ሥርዓቶች ቴህራን ኮም እና አልቫዝ ከተሞች ውስጥ ተካሂዶ ነበር። የዛሬውን አደጋ ተከትሎ የጄነራሉ ቀብር ለሌላ ጊዜ እንደተላልፈ ነው ዘገባዎቹ የጠቆሙት።

በዘንተኞች በዩናይትድ ስቴትስ ላይ የበቀል ዕርምጃ መወሰድ አለበት፤ ሲሉ መፈክሮች አሰምተዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG