በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምዕራባዊያን አገሮች ኢራን ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ ጣሉ


ፎቶ ፋይል፦ የኢራናውያን ተቃውሞ ሰልፍ
ፎቶ ፋይል፦ የኢራናውያን ተቃውሞ ሰልፍ

ዩናይትድ ስቴትስ ካናዳ እና አውስትሬሊያ ዛሬ ረቡዕ በኢራን ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ ጥለዋል፡፡ ባለስልጣናቱ ማዕቀቡ የተጣለባቸው ከሁለት ዓመታት በፊት ሂጃቧን በተገቢው መንገድ አልተከናነበችም ተብላ በኢራን የሥነ ምግባር ፖሊስ ቁጥጥር ስር በዋለችበት ህይወቷ ካለፈው ከማህሳ አሚኒ ሞት ተከትሎ የተቃውሞ ሰልፎችን በማፈን እና ሰዎችን በማሰር ተሳትፈዋል ተብለው ነው፡፡

በዛሬው ማዕቀብ ተቃዋሚ ሰልፈኞችን በመግደል እና በማሰር እንዲሁም ጋዜጠኞችን በማሰር የተወነጀሉ በርካታ ባለስልጣናት ተካትተዋል፡፡

አዲሱ ለውጥ አራማጁ የኢራን ፕሬዚደንት ማሱድ ፔዜሽኪያን በሥነ ምግባር ፖሊስ በሴቶች ላይ የሚፈጸመውን ወከባ እንደሚያስቆሙ በምርጫ ዘመቻቸው ላይ ቃል ቢገቡም ከማህሳ አሚኒ ሞትም ወዲህ ፖሊሶቹ ሴቶችን እና ልጃገረዶችን ሲያዋክቡ የሚያሳዩ ቪድዮዎች ወጥተዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG