በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራን ሳኡዲ አረብያ ላይ የደነቀችው የጥቃት አደጋ ያሳሰባቸው


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ

ኢራን ሳኡዲ አረብያ ላይ የደነቀችው የጥቃት አደጋ ያሳሰባቸው መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ተናገሩ፡፡

“ስጋቱ የደቀነው ገጽታ አሳስቦናል፡፡ በወታደራዊ፣ ዲፕሎማሲያዊና በሳኡዲ አረቢያ በሚገኙ የመረጃ መረቦቻችን በኩል ቋሚና ተከታታይ ግንኙነት እያደረግን ነው፡፡ የእኛን እና የአጋሮቻችንን ጥቅሞች ለማስጠበቅ የሚያስችለንን እርምጃ ለመውሰድ አናመነታም” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ትናትን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ከኢራን ሊሰነዘር ስለሚችለው ጥቃት ሳኡዲ አረብያ ለዩናይትድ ስቴትስ መረጃ ማጋራቷንም አሶሴይትድ ፕሬስ እና የዎል ስትሪ ጆርናል ትናንት ማክሰኞ ባወጡት ዘገባ አመልክተዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ባለሥልጣናት “በቀጠናው ያለው የስጋት ሁኔታ አሳስቧቸዋል” ስለተባለው ዘገባ የተጠየቁት የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀኔራል ፓት ራይደር በበኩላቸው፣ “ከሳኡዲ አረብያ አጋሮቻችን ጋር በዚያ በኩል ሊሰጡን

ስለሚችሉን መረጃ ምንነት በቋሚነት እየተገናኝን ነው” ሲሉ መልሰዋል፡፡ ራይደር አያይዘውም “ይሁን እንጂ ከዚህ በፊትም የተናገርነውን፣ አሁንም እደግመዋለሁ፤ ኃይሎቻችን በተሰለፉበት የትኛውም ስፍራ ኢራቅም ይሁን ሌላ የትም ቦታ ራሳችንን የመጠበቅና የመከላከል መብታችንን እናስከብራለን።” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG