በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ በኦሮምያ የ10.2 ቢሊዮን ብር መዋዕለ ንዋይ ፕሮጀክቶችን ይፋ አደረገች


የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት /ዩኤስኤድ/አማካይነት በኢትዮጵያ በኦሮምያ ክልል፣ 400ሺ በላይ ሰዎችን ኑሮ ሊያሻሽል የሚችል፣ በ10.2 ቢሊዮን ብር ሁለት አዳዲስ የመዋዕለ ንዋይ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡

በኢፋ/Iffa/ እና በዩኤስኤድ ተግባራዊ የሚደረጉ ሁለቱ የመዋዕለ ንዋይ ፕሮጀክቶች በኢትዮጵያ መንግሥት የሚመራውንና ዘጠኝ ሚሊዮን ሰዎች ራሳቸውን ከድህንነት እንዲያወጡ የሚያግዘውን የማኅበራዊ የምርት ደህንነት ወይም ሴፍቲኔት መርኃግብር እንደሚያጠናክር በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በመላው ኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች እየተካሄዱት ለሚገኙ ተመሳሳይ መርኃግብሮች ቀዳሚውን ድጋፍ እየሰጠ ያለው ዩኤስኤድ መሆኑን መግለጫው ጠቅሶ እኤአ ከ2015 ጀምሮ ወደ 60 ቢሊዮን ብር ማውጣቱን አስታውቋል፡፡

አሁን የሚካሄዱት ሁለቱ መርኃግብሮችም በዩናይትድ ስቴትስና በኢትዮጵያ መካከል የቆየውን ወዳጅነትና የጋራ ፍላጎት እንደሚያረጋግጡም መግለጫው አመልክቷል፡፡

በዚህ ሳምንት ውስጥ ይፋ የተደረጉት ሁለቱ ፕሮጀክቶች ዩኤስኤድ ባላፉት አምስት ዓመታት ውስጥ በ220 ቢሊዮን ብር ኢትዮጵያ ውስጥ ተግባራዊ እያደረጋቸው የሚገኙ ፕሮጀክቶች አካል መሆናቸውንም አመልክቷል፡፡

የሚሰጠው ድጋፍ በሁሉም አካባቢ ያሉ ኢትዮጵያውያን የተሻለ ጤናማና የበለጸገ ህይወት እንዲመሩ የሚያግዝ መሆኑንም በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ መግለጫ አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG