የአሜሪካ ስለላ ተቋማት፤ ሐማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት እንደሚሰነዝር የሚያሳይ መረጃው እንዳልነበራቸው፣ የዋይት ሃውስ ብሄራዊ የፀጥታ አማካሪ ጄክ ሰለቨን ትናንት አስታውቀዋል።
“እንዲህ ዓይነት ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል ከእስራኤላውያኑ የተሻለ መረጃ አልነበረንም” ሲሉ የፀጥታ አማካሪው ለዜና ሰዎች ተናግረዋል።
ሌሎች የዋይት ሃውስ ባለሥልጣናት እንዳሉት ሁሉ፣ ባለፈው ቅዳሜ የተፈፀመውን ጥቃት ከኢራን ጋር በቀጥታ የሚያያይዝ ነገር የአሜሪካ መንግስት እንዳላገኘ ሰለቨን ገልጸዋል።
“ኢራን ሐማስን በመርዳት በኩል አጠቃላይ ሚና ቢኖራትም፣ በተላይ ባለፈው ቅዳሜ የተፈጸመውን ጥቃት በተመለከተ ግን መረጃ የለንም” ብለዋል ሰለቨን።
እስራኤልን መርዳት በተመለከተ ለም/ቤቱ የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግ ጥያቄ እንደሚያቀርቡ፣ ዩክሬንን መርዳትን በተመለከተም እንዲሁ ጥያቄ እንደሚያቀርቡ ፕሬዝደንቱ ግልጽ አርገዋል ሲሉ ሰለቨን ጨምረው ገልጸዋል።
መድረክ / ፎረም