በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ደኅንነት መሥሪያ ቤቶች


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የቀጣይ አራት ዓመታት እቅዳቸውን ለመንደፍ እየሞከሩ ያሉት የዩናይትድ ስቴትስ ደኅንነት መሥሪያ ቤቶች ዓለም አሁን ከገጠማት ይበልጥ ውስብስብ ትርምስ ጋር ይጋፈጣሉ።

የቀጣይ አራት ዓመታት እቅዳቸውን ለመንደፍ እየሞከሩ ያሉት የዩናይትድ ስቴትስ ደኅንነት መሥሪያ ቤቶች ዓለም አሁን ከገጠማት ይበልጥ ውስብስብ ትርምስ ጋር ይጋፈጣሉ።

ዛሬ በዓለማችን ምዕራብ መራሹ ዓለምቀፍ ሥርዓት መዳከም ፈጣን የቴክኖሎጂ ለውጥ እየተካሄደ መሆኑና አስተማማኝነት የሌለው የፕሮዤዎች ማስፈፀሚያ ገንዘብ የማግኘት ዕጥረት የፈጠረው ችግር ሁኔታዎችን ይበልጥ አወሳስቧል ይላሉ - የዩናይትድ ስቴትስ ደኅንነት መሥሪያ ቤቶች።

ትላንት ይፋ በተደረገው ብሄራዊ የዩናይትድ ስቴትስ ደኅንነት የቀረበው ትልም ዝርዝር ይዟል።

ትልሙ “ከቀደመው ስትራቴጂ አስፈላጊ ሲሉ የገለፁት መሻሻል የታየበትና አስተማማኝ ባልሆነ ጊዜ የአሜሪካውያን ደኅንነት የተጠበቀ እንደሚሆን ዳግም ለማረጋገጥ የታለመ ነው” ብለዋል ከፍተኛ ባለሥልጣናቱ።

በሃገር ውስጥ እና በዓለምቀፍ ደረጃ ብርቱ ፈተናዎችን እንጋፈጣለን ያለው የዩናይትድ ስቴትስ የደኅንነት መሥሪያ ቤቶቹ ያቀረቡት ጥናት - አሁን ያለውን ማዕበልና ውስብስብ የዓለም ሁኔታ በጥንቃቄ ለማለፍ ነገሮችን ከቀድሞው በተለየ መልክ መሥራት ይጠበቅብናል ሲል አስገንዝቧል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG