በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ያፈተለከው የዩናይትድ ስቴትስ “የጦር ርዳታ መረጃ” ደቡብ ኮሪያን አወካት


የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ መሥሪያ ቤት
የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ መሥሪያ ቤት

ዩናይትድ ስቴትስ፣ የረጅም ጊዜ አጋሯ የኾነችውን የደቡብ ኮሪያ “ከፍተኛ የደኅንነት ባለሥልጣናት ትሰልላለች፤” በሚል ያፈተለከ መረጃ፣ በአሜሪካ ብዙኃን መገናኛዎች መሠራጨቱን ተከትሎ፣ በኹለቱ ሀገራት መሀከል የተፈጠረውን ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ቀውስ ለመቆጣጠር፣ የደቡብ ኮሪያ መንግሥት እየጣረ መኾኑ ተነገረ፡፡

የግንኙነት ቀውሱ የተከሠተው፣ በደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ውስጥ፣ ለዩክሬን የጦር መሣሪያ ስለ መስጠት የተደረገውን ውይይት ዝርዝር የያዘው የዩናይትድ ስቴትስ ማስታወሻ፣ ሰሞኑን ሾልኮ በብዙኃን መገናኛዎች ከወጣ በኋላ ነው፡፡

“ሾልኮ ወጥቷል” የተባለውን ሰነድ አግኝቶ ባለፈው እሑድ ያተመው፣ ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ እንደኾነም ተመልክቷል፡፡

የደቡብ ኮሪያ ብሔራዊ የደኅንነት ምክትል አማካሪ ኪም ቴ ህዮ፣ “መረጃው ይፋ ከተደረገ ወዲህ፣ በውስጣችን ያለውን ኹኔታ ገምግመናል፡፡ ዩናይትድ ስቴትስም የራሷን ምርመራ አድርጋለች፡፡ የኹለቱ አገሮች መከላከያ ሚኒስትሮች፣ ዛሬ ጧት በስልክ ተገናኝተው በመነጋገር፣ ስለ ክሥተቱ ያላቸው አቋም ተመሳሳይ እንደኾነ ተገናዝበዋል፤” ብለዋል፡፡

ኪም አያይዘውም፣ ከተለቀቁት መረጃዎች የሚበዙት “የተፈበረኩ” እንደኾኑና መረጃዎቹ የተገመገሙበት ኹኔታ ግን “ወጥነት እንዳለው” ጠቅሰዋል፡፡ ለዩናይትድ ስቴትስ፣ ክሥተቱ የአገር ውስጥ ጉዳይ እስከኾነ ድረስ፣ የአገሪቱ ፍትሕ ሚኒስቴር እንደሚመረምረውና ይህ ደግሞ የተወሰነ ጊዜ እንደሚወስድ ኪም አመልክተዋል፡፡

በደቡብ ኮሪያ ላይ ያተኮረው ያፈተለከው መረጃ፣ ይፋ ያደረገው አስገራሚም ኾነ ጎጂ መረጃ እንደሌለው ተገልጿል፡፡ ይኹን እንጂ፣ ስለ “ሲግናል ኢንተለጀንስ” በመረጃው የተነሣው ጉዳይ፣ ዋሽንግተን፥ በጣም አስፈላጊዋ ከኾኑ አጋሮችዋ አንደኛውን እንደምትሰልል የሚጠቁም ነው፤ ተብሏል፡፡

በአፈተለከው መረጃ የተከሠተው ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ቀውስ፣ በዚኽ ወር መጨረሻ፣ ዩናይትድ ስቴትስን ለመጎብኘት ወደ ዋይት ኀውስ ለመምጣት በዝግጅት ላይ ለሚገኙት፣ የደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት ዩን ሱክ ዬኦል፣ አዳጋች ኹኔታ ሊፈጥርባቸው እንደሚችል ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG