በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩስያ፣ ቻይናና ኢራን በዩናይትድ ስቴትስ የምርጫ ሂደት ውስጥ ጣልቃ እየገቡ መሆናቸው ተገለጸ


የብሄራዊ ጸረ ስለላና የጸጥታ ጥበቃ ማእከል ስራ-አስኪያጅ ዊልያም ኢቫኒና በተናገሩት መሰረት፣ ሶስቱ ሀገሮች ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ መከፋፈል እንዲኖርና የሀገሪቱ ህዝብ በዲሞክራስያዊው ሂደት ላይ ያለው እምነት እንዲሸረሸር እሰሩ ናቸው።

ነገር ግን ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በመጪው ህዳር ወር በሚካሄደው ምርጫ ፕረዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወይስ ዲሞክራቱ ተወዳዳርያቸው ጆ ባይደን በሚለው ላይ ሩስያ፣ ቻይናና ኢራን የተከፋፈሉ መሆናቸውን ኢቫኒና ጠቁመዋል።

ሩስያ ዲሞክራቱን ለፕረዚዳንትነት አየተደዳደሩ ያሉትን ጆ ባይደንን ማንቋሸሽ ላይ እየሰራች መሆንዋን፣ አንዳንድ ከሩስያ መንግስት ጋር የተሳሰሩ ወገኖች የትራምፕን የምርጫ ውድድር በሩስያ ቴሌቪዥንና በማህበራዊ ሚድያ እያሞጋገሱ መሆናቸውን ባለስልጣኑ ጠቁመዋል።

ቻይናና ኢራን በበኩላቸው ባይደን እንዲመረጡ የሚረዱ እንደሚመስሉ ኢቫኒና አክለው ገልጸዋል።

ፕረዚዳንት ዶናልድ ትርምፕ ወደ ሁዋላ ሲናገሩ፣ “ሩስያ እንዲመረጥ የማትፈልገው ስው ቢኖር ዶናልድ ትራምፕ ነው። ምክንያቱም በሩስያ ላይ ካባድ አቋም በመያዝ በኩል እንየን የሚያክል የለም” ብለዋል።

XS
SM
MD
LG