በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ሶሪያና ኡጋንዳ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ ማዕቀብ ጣለች


ዩናይትድ ስቴትስ በትናንትናው እለት ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰት ይፈጽማሉ ባለቻቸው በኢራን ሶሪያና ኡጋንዳ በሚገኙ በርካታ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ ማእቀብ መጣሏን አስታወቀች፡፡

ማእቀቡ የወጣው የዲሞክራሲ ጉባኤ የሚደረግበትን ሳምንት ምክንያት በማድረግ መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ማዕቀቡ ዴሞክራሲ ስርዐትን በማለክበር፣ ጭቆናን አስፍነዋል፣ ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን አፍነዋል ከተባሉት፣ እንደ ኢራን እንዲሁም የኬሚካላዊ የጦር መሳሪያዎችን በሰላማዊ ዜጎች ላይ ተጠቅመዋል ከተባሉት እንደ ሶሪያ ካሉ አገሮች ጋር የተሳሰሩ ግለሰቦችና ተቋማትን፣ ኢላማ ያደረገ መሆኑን መግለጫው አመልክቷል፡፡

የማእቀቡ ውሳኔ፣ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ያሉትንና፣ በማእቀቡ ውስጥ የተካታተቱን የግለሰቦችን ሀብት በሙሉ የሚያግድ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በማዕቀቡ ውስጥ ከተካተቱት ግለሰቦች ውስጥ፣ የዩጋንዳው የወታደራዊ ደህንነት ኃላፊ ሜጀር ጀኔራል አቤል ካንዲሆ የሚገኙበት ሲሆን፣ ማእቀቡ የተጣለባቸው በሳቸው አስተዳደር ሥር በተፈጸሙ የሰአብዊ መብት ጥሰቶች መሆኑ በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

XS
SM
MD
LG