በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ ቪዛ ቀጠሮ “እጅግ ተጓትቷል” ተባለ


የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት
የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት

ለጉብኝት ወይም ለሥራ ወይም ለመኖር ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ቪዛ የሚጠይቁ አመልካቾች ከ1994ቱ የሽብር ጥቃት ወዲህ “እጅግ የተራዘመ” ቀጠሮ እንደሚሰጣቸው ሰሞኑን የወጡ የሃገሪቱ የውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት መረጃዎች ጠቁመዋል።

አንዳንድ ዓለምአቀፍ ተጓዦች የቪዛ ቃለ መጠይቅ ቀጠሮ ለማግኘት ከስድስት ወር እስከ አንድ ዓመት እንደሚፈጅባቸው ተናግረዋል።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የአሜሪካ ኤምባሲዎች ለሁለት ዓመታት መዘጋታቸውና ቪዛ ‘መስጠት ማቆማቸው የፈጠረው ችግር ነው’ ሲሉ በካቶ ኢንስቲትዩት የስደተኞች ፖሊሲ ኃላፊ ዴቪድ ቤየር ለቪኦኤ ተናግረዋል።

“በወረርሽኙ ምክንያት የተከማቸ ሥራ አለ፤ ከአንድ ዓመት በላይ ቀጠሮ ያስፈለገውም ለዚሁ ነው” ብለዋል ዴቪድ ቤየር።

የቀጠሮ ርዝመት ከኤምባሲ ኤምባሲ ቢለያይም ‘አሁን ያለው ሁኔታ ግን ከ1994ቱ የሽብር ጥቃት ወዲህ የከፋ ነው’ ብለዋል ቤየር።

ከጥቃቱ ሁለት ዓመታት በኋላ ጉዳይ ለማስፈፀም የሚወስደው ጊዜ ሦስት ሳምንት ያህል እንደነበር አንድ የውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ኃላፊ በወቅቱ ለአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ተናግረው ነበር።

የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ሠንጠረዥ እንደሚያሳየው ለአንዳንድ ቪዛ አመልካቾች ቃለ መጠይቅ ለማደረግ ከአንድ ዓመት በላይ ሲወስድ የንግድና የጉብኝት ቪዛ አመልካቾች ደግሞ ከስድስት ወራት በላይ እንደሚጠብቁ ተገልጿል።

ዩናይትድ ስቴትስ ለ40 ሃገሮች ተጓዦች ያለ ቪዛ ገብተው ለዘጠና ቀናት እንዲቆዩ ትፈቅዳለች።

XS
SM
MD
LG