በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ የፍልሰተኞችን ሕግ ጠበቅ ለማድረግ ዝተዋል


ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ
ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ

ዋይት ሃውስ እና የሁለቱ ፓርቲዎች የሕግ መወሰኛ ም/ቤት ዓባላት በጋራ ሲደራደሩበት የቆየውንና ለዩክሬን፣ እስራኤልና ታይዋን የ106 ቢሊዮን ዶላር ለመስጠት እንዲሁም የፍልሰተኞችን ደንብ ጠበቅ ለማድረግ ለወራት ሲሰራበት የቆየውን ስምምነት እንደሚቃወሙ፣ የሪፐብሊካን እጩ እንደሚሆኑ የሚጠበቁት የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ በመግለጽ ላይ ናቸው።

በቀጣዩ ምርጫ የፍልሰተኞች ጉዳይ አንገብጋቢ እንደሆነ በሚያምኑ ድምጽ ሰጪዎች የሚደገፉት ትረምፕ፣ ባለፈው ማክሰኞ በኒው ሃምፕሸር የተደረገውን ቅድመ ምርጫ አሸንፈዋል።

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ አገራችን በመጉረፍ ላይ ናቸው። የሚመጡትም፣ ከእስር ቤት እና ከአዕምሮ ሕክምና ተቋማት ነው”

“በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ አገራችን በመጉረፍ ላይ ናቸው። የሚመጡትም፣ ከእስር ቤት እና ከአዕምሮ ሕክምና ተቋማት ነው” ሲሉ ተደምጠዋል ትረምፕ፡፡

ትረምፕ ማክሰኞ ዕለት የተቀዳጁት ድል፣ የሪፐብሊካን ሕግ አውጪዎች የፍልሰተኞችን ሕግ በተመለከተ ሰጥቶ በመቀበል ላይ የተመሠረተ ስምምነት እንዳያደርጉ ጫና ለማሳደር ይረዳቸዋል ተብሏል።

ትረምፕ በባለቤትነት በያዙት የማኅበራዊ መድረክ “ትሩዝ ሶሻል” ላይ ባወጡት መልዕክት፣ “በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ሰዎች እየተፈጸመ ያለ ወርራ” ብለው የገለጹትን የፍልሰተኞች ወደ አገሪቱ መግባት ለማስቆም የሚያስችሉ ሁኔታዎች ካልተካተቱ፣ ሪፐብሊካኖች በድንበር ሕጉ ላይ ስምምነት እንዳያደርጉ አሳስበዋል።

ዋይት ሃውስ እና የሁለቱ ፓርቲዎች የሕግ መወሰኛ ም/ቤት አባላት ለወራት በጋራ ሲደራደሩበት የቆየውና ለዩክሬን፣ እስራኤልና ታይዋን የ106 ቢሊዮን ዶላር ርዳታ ለመስጠት ያለመው ስምምነት፤ የፍልሰተኞች ደንብ ጠበቅ የሚልበት እና ድንበርንም ለመጠበቅ የሚያስችሉ ሁኔታዎች እንዲካተትበት ሪፐብሊካኖች በመወትወት ላይ ናቸው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG