በመጪው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የሪፐብሊካን ፓርቲው ዕጩ እንደሚሆኑ የሚጠበቁት የቀድሞው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ የውጭ ርዳታ እንዲለቀቅ እና የኢሚግሬሽን ደንቦች እንዲጠብቁ የሚያደርገው ስምምነት ዳር እንዳይደርስ ሊያደናቅፉ ተነስተዋል፡፡
ለዩክሬን ለእስራኤል እና ለታይዋን ድጋፍ የሚውል የ106 ቢሊዮን ዶላር የውጭ እርዳታ የሚያስፈቅደው እና የሀገሪቱን የኢሚግሬሽን ደንቦች የሚያጠብቀውን ስምምነት ለመቋጨት ኋይት ሐውስ እና የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ዲሞክራት እና ሪፐብሊካን አባላት ለወራት ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡
የቪኦኤ የኋይት ሐውስ ቢሮ ዋና ዘጋቢ ፓትሲ ዊዳኩስዋራ ያጠናቀረችውን ዘገባ ቆንጅት ታየ ታቀርበዋለች፡፡
መድረክ / ፎረም