በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አውሎ ነፋስ “ሚልተን” በፍሎሪዳ ከፍተኛ ሥጋት ፈጥሯል


በአሜሪካ ደቡባዊ ምሥራቅ ክፍል የምትገኘውን የፍሎሪዳ ግዛት፣ “ሚልተን” በሚል የተሰየመ አደገኛ አውሎ ነፋስ የቀላቀለ ዝናብ ሊመታት እየተቃረበ መሆኑ ተነግሯል።

ለሕይወትም አደገኛ እንደሆነ የተነገረው አውሎ ነፋስ ዛሬ ምሽት ወይም ነገ ሐሙስ ማለዳ የፍሎሪዳ ማዕከላዊ ምዕራብ ባህር ዳርቻን ይመታል ብለው እንደሚጠብቁ የአየር ትንበያ ባለሙያዎች ተናግረዋል።

ትላንት ማክሰኞ ፍጥነቱ በሰዓት 260 ኪ.ሜ. እንደሆነ የተመዘገበው ነፋስ የውቅያኖሱን ውሃ ወደ መሬት ስለሚገፋው የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ሥጋት ፈጥሯል።

3.3 ሚሊዮን ሕዝብ የሚኖርባትን ታምፓ ቤይ ከተማን ጨምሮ ማዕከላዊ ምዕራብ ፍሎሪዳን ይመታል የተባለው አውሎ ነፋስ ከ3 እስከ 4.5 ሜትር ከፍታ ያለው ውሃ ሊፈጥር እንደሚችል ተገምቷል። ከተማይቱ በአውሎ ነፋስ ስትመታ ከእ.አ.አ 1921 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል።

በምዕራብ ፍሎሪዳ 500 ኪ.ሜ. ርዝመት ለሚሸፍነው ባሕር ዳርቻ ከዛሬ ጀምሮ ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ነፋስ እንደሚኖር ማስጠንቀቂያ ተላልፏል።

በአስገዳጅነትም ይሁን በፈቃደኝነት ሰዎች ቤታቸውን ጥለው እንዲወጡ በመጠየቁ መንገዶች በተጓዦች ተጨናንቀው ሲስተዋሉ በርካታ የነዳጅ ማዲያዎችም ነዳጃቸውን በመጨረሳቸው እጥረት ተፈጥሯል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG