በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ በሁቲ የተተኮሱ ድሮኖችና አንድ ሚሳዬልን አወደመች


የየመን ካርታ
የየመን ካርታ

ከሁቲ አማፂያን ተተኩሰው የነበሩ ድሮኖችን እና አንድ ሚሳዬልን በቀይ ባሕር ላይ ማውደሟን አሜሪካ አስታውቃለች፡፡

ቦምብ የተሸከሙት ድሮኖች እና ፀረ መርከብ ባሊስቲክ ሚሳዬሉ ተነጣጥረው የነበሩት በአካባቢው በምትገኘው እና በሁቲ ላይ በሚደረገው ድብደባ ላይ በመሳተፍ ላይ ባለችው ‘ዩኤስኤስ ካርኔ’ በተሰኘችው አውዳሚ መርከብ ላይ ነበር።

የእስራኤል እና ሐማስ ጦርነት መፈንዳቱን ተከትሎ፣ በኢራን ይደገፋሉ የሚባሉት የየመን ሁቲ አማፂያን በቀይ ባሕር ላይ በሚመላለሱ መርከቦች ላይ ጥቃታቸውን አፋፍመዋል።

ዛሬ ረቡዕም በአንድ መርከብ ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ታውቋል።

አሜሪካ በአየር ባደረሰችው ጥቃት ቦምብ የተሸከሙት ድሮኖች እና ፀረ መርከብ ባሊስቲክ ሚሳዬሉ መደምሰሳቸውን የአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ አስታውቋል።

የሁቲ ወታደራዊ ቃል አቀባይ የሆኑት ብርጋዴር ጄኔራል ያህያ ሳሪ ጥቃቱ መፈጸሙን አምነው፣ ኃይሎቻቸውም ሁለት የአሜሪካ የጦር መርከቦችን ኢላማ አድርገው እንደነበር፣ ዝርዝር መረጃ ሳይሰጡ አስታውቀዋል።

“በጋዛ በሚገኙት ፍልስጤማውያን ላይ የተፈጸመው ወረራ እና ከበባ እስከሚቆም ሁቲዎች ጥቃታቸውን አያቆሙም” ሲሉ ጄኔራሉ ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG