በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፈጉባኤዋ ፐሎሲ በሳኡዲ ተፈጽሟል የተባለውን የማሰቃየት ተግባር አወገዙ


ዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ፣ ናንሲ ፐሎሲ
ዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ፣ ናንሲ ፐሎሲ

በሳኡዲ አረብያ የእርዳታ አገልግሎት ሠራተኛ በነበረው አብዱርሃማን አል ሳድኻን ላይ ተፈጽሟል የተባለው የማሰቃየት ተግባር፣ በእጅጉ ያሳሳበቸው መሆኑን፣ ዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ፣ ናንሲ ፐሎሲ ትናንት እሁድ በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉ መልክት አስታወቁ፡፡

ፕሎሲ በመልዕክታቸው “የይግባኝ ችሎቱን ሂደትም ሆነ የሳኡዲ አረብያን የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ምክር ቤቱ በቅርበት ይከታተላል ብለዋል፡፡

አብዱርሃማን እኤአ መጋቢት 2018 በሳኡዲ ባለሥልጣናት ትዕዛዝ የታሰረ ሲሆን 20 አመታት እስራትና የ20 ዓመታት የጉዞ ማዕቀብ የተፈረደበት መሆኑን እኤአ ሚያዝያ 6 የወጣው የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ አስታውቋል፡፡

መቀመጫውን በጄኔቭ ያደረገና መና የተባለው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድን ባላፈው ሚያዝያ ባወጣው መግለጫ አል ሳድኻን የተከሰሰው ሁለት ምጸታዊ ይዘት ያላቸውን የትዊተር አካውንት ይመራል አይሲስ ከተባለው የሽብርተኞች ቡድንን ይደግፋል፣ የሚያስተላልፋቸውም መልዕክቶች “የህዝብና ሀይማኖታዊ ሥር ዓትና እሴቶችን የሚቃወሙ ናቸው” የሚል ነው፡፡

አልሳድኻን የግርፋት በኤሌክትሪክ ንዝረት ማሰቃየት የተካሄደበትና በድብደባም ስብራት የደረሰበት መሆኑም ተመልክቷል፡፡ በልኡል መሀመድ ቢን አልሳማን የምትመራው ሳኡዲ አረብያ በበርካታ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የምትጠቀስ አገር መሆኗም በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

XS
SM
MD
LG