በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሪፐብሊካን የም/ቤት አባላት ኢኻን ኦማርን ከኮሚቴው አባልነት አነሷቸው


የዴሞክራቲክ ፓርቲ ተወካይ ኢኻን ኦማር
የዴሞክራቲክ ፓርቲ ተወካይ ኢኻን ኦማር

የዴሞክራቲክ ፓርቲ ተወካይ ኢኻን ኦማር፣ ስለ እስራኤልና በዋሽንግተንም ስላላት ተጽእኖ በሰጡት አስተያየት፣ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ሪፐብሊካን እንደራሴዎች በሰጡት ድምጽ፣ ከምክር ቤቱ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ አባልነት እንዲነሱ አደረጉ፡፡

የሶማሊያ ተወላጅና ሙስሊም የሆኑትን ህግ አውጭ እንደራሴዋን፣ ከኮሚቴው አባልነት የማንሳቱ ውሳኔ የመጣው፣ ባላፈው የምክር ቤቱ ዘመን፣ ዴሞክራቶች፣ ቀኝ አክራሪ ህግ አውጭዎችን፣ በሰጡት የሁከትና የአመጽ አስተያየት ከኮሚቴዎች ማሰናበታቸውን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከኮሚቴው የመነሳታቸው ድምጽ ከተሰጠ በኋላ ኦማር በሰጡት አስተያየት “ወደ ምክር ቤቱ የመጣሁት ዝም ለማለት አይደለም፡፡ ወደ ምክር ቤቱ የመጣሁት የእነሱ ድምጽ ልሆን ነው፡፡

በዚህ ኮሚቴ ውስጥ ለአንድ ዙር አባል ባልሆን ድምጼም ሆነ መሪነቴ አይቀንስም፡፡ ድምጼ ከፍ እያለና እየጠነከረ፣ መሪነቴም እንደ ቀድሞው ሁሉ በዓለም ዙሪያ እንደተከበረ ይቀጥላል፡፡ ስለዚህ ድምችሁን ሰጣችሁም ነፈጋችሁም!” ብለዋል፡፡

ኦማር አያይዘውም “እኔ እዚሁ እቆያለሁ፡፡ እኔ እዚህ የመጣሁት በዓለም ዙሪያ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመቃወምና ለተሻለ ዓለም ለመሟገት ነው” ብለዋል፡፡

የህዝብ እንደራሴዋ ኦማር በአፍሪካ ጉዳይ በሚያተኩረው የውጭ ጉዳዮች ንኡስ ኮሚቴ፣ ከፍተኛዋ የዴሞክራቲክ አባል እንዲሆን ታቅዶ ነበር፡፡

በተወካዮቹ ምክር ቤቱ የዴሞክራቲክ መሪ የኒውዮርኩ ተወካይ ሃኪም ጀፍሪ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለሚታተመው ፖለቲኮ በሰጡት አስተያየት “ተጠያቂነት ነበር በዚያ መሠረት ኢኻን ኦማር ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡

ከስህተታቸውም እንደሚማሩ ጠቁመዋል፡፡ ድልድይ ለመገንባት እንዲመሰሩ ተናግረዋል ምክያቱም ድልድይ በመስራት ነው የምናምነው እንጂ ግንብ በመስራት አይደለም፡፡” ሲሉ የኦማርን ከኮሚቴው መነሳት አግባብ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG