በጠንካራ አቋማቸው የሚታወቁት የአሜሪካ ምክርቤት አባል ማርጀሪ ቴይለር ግሪን ረቡዕ እለት አፈ-ጉባዔውን ማይክ ጆንሰንን ከስልጣን ለማንሳት ድምፅ እንዲሰጥ ቢጠይቁም፣ የህግ አውጪዎቹ ጥያቄውን በፍጥነት ውድቅ አድርገዋል።
በምክርቤቱ ውስጥ ጠንካራ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፍ መሆናቸው የሚነገርላቸው ግሪን በምክርቤቱ ፊት ቆመው፣ ጆንሰን አፈጉባዔ ሆነው ባገለገሉበት ወቅት ፈጸሟቸው ያሏቸውን የሕግ ጥሰቶች የያዘ ረጅም ዝርዝር ባነበቡበት ወቅት፣ ባልደረቦቻቸው የተቃውሞ ድምፅ አሰምተዋል።
ግሪን። የጆንሰንን አመራር "አሳዛኝ፣ ደካማ እና ተቀባይነት የሌለው" ሲሉም ተችተዋል።
ሪፐብሊካኖች ከራሳቸው ፓርቲ የተመረጡትን አፈ-ጉባዔ ለማንሳት ሲሞክሩ በወራት ውስጥ ሁለተኛ ጊዜያቸው ሲሆን በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ ያልታየ እና በፓርቲ ግርግር ውስጥም ያልተለመደ መሆኑ ተገልጿል።
ሪፐብሊካን ሕግ አውጪዎች ጆንሰንን ስለተፈጠረው ነገር በማፅናናት ድጋፋቸውን አረጋግጠውላቸዋል።
መድረክ / ፎረም