በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ም/ቤት የ1.3 ትሪልዮን ዶላር በጀት ለመመደብ ድምፅ መስጠት ይጀምራሉ


የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት መሪዎች የ1.3 ትሪልዮን ዶላር በጀት ለመመደብ ዛሬ ድምፅ መስጠት ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል። የምክር ቤቱ አባላት ተደራዳሪዎች ትላንት ማታ አፅድቀውታል።

የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት መሪዎች የ1.3 ትሪልዮን ዶላር በጀት ለመመደብ ዛሬ ድምፅ መስጠት ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል። የምክር ቤቱ አባላት ተደራዳሪዎች ትላንት ማታ አፅድቀውታል።

የምክር ቤት አባላት በያዝነው ዓመት የመንግሥት ሥራ ለሦስተኛ ጊዜ መዘጋትን ለማስወገድ እስከ ነገ እኩለ ሌሊት ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ማፅደቅ ይኖርባቸዋል።

የህግ መመሪያው ምክር ቤት የበጀቱን ህግ ዛሬ ያፀደቀዋል ተብሎ ይጠበቃል። የህግ መወሰኘው ምክር ቤት ደግሞ የጊዜው ገደብ ከመድረሱ በፊት ያፀድቀዋል የሚል እምነት አለ።

የበጀቱ እቅድ የመንግሥትን ሥራ እስከ መጪው መስከረም ወር ባለው ጊዜ ለማንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግና ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እንደሚደግፉት ትላንት የዋይት ኃውስ መግለጫ ጠቁሟል።

ይህ በጀት በዩናይትድ ስቴትስና በሜክሲኮ ድንበር ላይ ለሚተከል አጥር 1.6 ቢልዮን ዶላር መጪን ያካትታል። ትራምፕ ግንብ ለመሥራት የጠየቁት ግን 25 ቢልዮን ዶላር ነበር።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG