በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ሕገ ወጥ ስደተኞች በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ የሚያዝ ሕግ አጸደቀ


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ ሴናተር ኬቲ ብሪት የሌከን ራይሊ ሕግ ገና ሀሳብ በነበረበት ወቅት ንግግር እያደረጉ፤ በዋሽንግተን፣ ዲሲ፤ እአአ ጥር 9/2025
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ ሴናተር ኬቲ ብሪት የሌከን ራይሊ ሕግ ገና ሀሳብ በነበረበት ወቅት ንግግር እያደረጉ፤ በዋሽንግተን፣ ዲሲ፤ እአአ ጥር 9/2025

ምክር ቤቱ በትላንትናው ዕለት ያጸደቀው ይህ ሕግ በስርቆት እና በጥቃት ወንጀሎች የተከሰሱ እና የመኖሪያ ፍቃድ የሌላቸው ጥገኝነት ጠያቂዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ የሚያዝ ነው። ይህም ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሕገ ወጥ ስደትን ለመቆጣጠር ለያዙት ዕቅድ በፍጥነት ዳር መድረስ፣ መጠነኛም ቢሆን የሁለቱንም ፓርቲዎች አባላት ድጋፍ አግኝቶ የጸደቀ የመጀመሪያው ሕግ አድርጎታል።

ባለፈው ዓመት በአንድ የቬንዙዌላ ተወላጅ የሆነ ስደተኛ በተገደለችው የጆርጂያ ክፍለ ግዛቷ የነርስነት ሞያ ትምህርት በመከታተል ላይ የነበረች ወጣት ስም የተሰየመው እና ‘የሌከን ራይሊ ሕግ’ የሚል ሥያሜ የተሰጠው ይህ ድንጋጌ፤ ትራምፕ በፕሬዝዳንታዊው ምርጫ አሸናፊ ሆነው መውጣታቸውን ተከትሎ ‘በኢሚግሬሽን ጉዳዮች ዙሪያ የሚካሄደው የፖለቲካ ክርክር የቱን ያህል ወደ ቀኝ እያዘመመ መሆኑን የሚያሳይ ነው’ ተብሏል።

የኢሚግሬሽን ፖሊሲ ጉዳይ በምክር ቤቱ ሁለቱን ፓርቲዎች ጎራ ለይቶ ለረዥም ጊዜ ሲያወዛግብ የቆዩ ጉዳየ ቢሆንም፣ የፖለቲካ እጣቸው የሚያሳስባቸው 46 ዲሞክራቶች ወሳኝ መሆኑ የተነገረለትን እቅድ 263 ለ156 በሆነ ድምጽ ለማጽደቅ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላትን ተቀላቅለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG