በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እንደራሴዎች ትራምፕ እንዲከሰሱ ለሚጠይቀው የክስ አንቀጽ ቃለ መሐላ ይፈፅማሉ


የዩናይትድ ስቴትስ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደራሴዎች
የዩናይትድ ስቴትስ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደራሴዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደራሴዎች የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንዲከሰሱ ላስገቡት የክስ አንቀፅ ዛሬ ቃለ መሐላ ይፈፅማሉ። እንደራሴዎቹ ትላንት ምሽት ወደ ምክር ቤቱ አምርተው የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሕገወጥ መንግደ ስልጣን ላይ ለመቆየት ሲሉ ምርጫው ተጨበርብሯል በማለት ደጋፊዎቻቸው የምክር ቤቱን ሕንፃ ወረው ጥቃት እንዲፈጽሙ አድርገዋል በሚል የቀረበውን የክስ አንቀፅ በይፋ ለመወሰኛ ምክር ቤቱ አስገብተዋል።

ዶናልድ ትራምፕ በደቦ የተደራጁ ጥቃት አድራሾች ምክር ቤቱን እንዲወሩ በማነሳሳት እጃቸው እንዳለበትም ተጠቅሷል። በዚህ በእርሳቸው አነሳሽነት በተፈፀመው ጥቃትም ለአምስት ሰዎች ሕይወት ማለፍ ምክኒያት ሆኗል።

የትራምፕ ክስ በይፋ የሚታይበት ግዜ በዴሞክራቶች እና ሪፐብሊካኖች ውይይት ተደርጎበት ለዐቃቤ ሕግ እና ለትራምፕ ተከላካይ ጠበቆች የዝግጅት ጊዜ ለመስጠት እንዲቻል በሚል የካቲት 1/2013 ዓ.ም እንዲጀመር ቀነ ቀጠሮ ተቆርጦለታል።

XS
SM
MD
LG