በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ በሱስ አስያዥ ዕጾች ዝውውር የተወነጀሉት የቀድሞ የሁንዱራስ ፕሬዚዳንት ተላልፈው ይሰጡኝ አለች


የቀድሞው የሁንዱራስ ፕሬዚዳንት ሁዋን ኦርላንዶ ሄርናንዴዝን ሁንዱራስ
የቀድሞው የሁንዱራስ ፕሬዚዳንት ሁዋን ኦርላንዶ ሄርናንዴዝን ሁንዱራስ

ዩናይትድ ስቴትስ በህገ-ወጥ ሱስ አስያዥ አደገኛ መድሃኒቶች እና ዕጾች አዘዋዋሪዎነት የምትጠረጥራቸውን የቀድሞውን የሁንዱራስ ፕሬዚዳንት ሁዋን ኦርላንዶ ሄርናንዴዝን ሁንዱራስ አሳልፋ እንድትሰጣቸው በኦፊሴል ጠየቀች።

የሆንዱራስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ትላንት ሰኞ በትዊተር ገፁ ላይ እንዳሰፈረው ቴጉሲጋልፓ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ የቀድሞው መሪ ለአሜሪካ ተላልፈው እንዲሰጡ ይፋ ጥያቄ አቅርቧል።

ሄርናንዴዝ ተላልፈው እንዲሰጡ የሚፈለጉ ፖለቲከኛ መሆናቸው በተነገረበት ወቅት ሲኤንኤን የቴሌቭዥን ጣቢያ ጥያቄውን ያዘሉ ምስሎች በማሳየት ላይ ነበር።

በሆንዱራስ ዋና ከተማ ቴጉሲጋላፓ በርካታ ፖሊሶች የቀድሞውን ፕሬዚደንት መኖሪያ ቤት መክበባቸው ተዘግቧል። የሃገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም በዛሬው ዕለት በቀድሞው ፕሬዚዳንት ላይ የቀረበውን ተላልፈው ይሰጡኝ በሚለው የዩናይትድ ስቴትስ ጥያቄ ጉዳይ የሚያስችል ዳኛ ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን በቅርቡ “ሄርናንዴዝ" ሙስና በመፈጸም ወይም እንዲፈጸም በመርዳት በከፍተኛ የሙስና ተግባር እየተሳተፉ እና ሱስ አስያዥ አደገኛ መድሃኒቶች እና እጾችን በማዘዋወር ሥራ ተሰማርተዋል። ከዚያ የሚገኘውን ገቢም ለፖለቲካ ዓላቸው ማጽፈጽሚያነት እየተጠቀሙበት መሆኑን የሚያረጋግጡ ተዓማኒነት ያላቸው መረጃዎች አሉ” ሲሉ ተደምጠዋል።

ወንድማቸው የቀድሞው የሆንዱራስ ምክር ቤት አባል ቶኒ ሄርናንዴዝ ባለፈው ዓመት ነው፤ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሱስ አስያዥ አደገኛ መድሃኒቶች እና እጾች ሕገ ወጥ ዝውውር ተወንጅለው የዕድሜ ልክ እስራት የተፈረደባቸው።

የቀድሞው የሄንዱራስ ፕሬዚዳንት ባለፈው ጥር 20, 2014 ዓም በእርሳቸው እግር የተተኩት ዚዮማራ ካስትሮ የመጀመሪያዋ የሁንዱራስ ሴት ፕሬዝዳንት ከሆኑ ጥቂት ሰዓታት በኋላ ነበር

የመካከለኛ አሜሪካይቱ ሃገር የፓርላማ አባል ሆነው ቃለ መሃላ የፈፀሙት። ጠበቃቸው የሸንጎ አባል በመሆናቸው ያለመከሰስ እና ተላልፎ ያለመሰጠት መብት አላቸው” ሲሉ ይከራከራሉ።

XS
SM
MD
LG