በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ሴቴትስ ጠ/ፍ ቤት በባይደን የክትባት ትዕዛዝ ውሳኔ ሰጠ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን

የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ፕሬዚዳንት ባይደን፣ ከ100ና ከዚያ በላይ ሠራተኞ ያላቸው የንግድ ድርጅቶች ሰራተኞቻቸውን የኮቪድ-19 ክትባት መውሰዳቸውን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል በሚል ያወጡትን ትዕዛዝ ትናንት ሀሙስ በሰጠው ውሳኔ ውድቅ አደረገው፡፡

በሌላም በኩል ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ፣ የፌዴራል መንግሥቱን ድጎማ በሚወስዱ የጤና ተቋማት የሚሰሩ ሠራተኞች ክትባቱን መውሰድ ግዴታ ያለባቸው መሆኑን በማጽደቅ ወስኗል፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደን የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አስመልክቶ ትናንት በሰጡት መግለጫ “ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በሳይንስም ሆነ በህግ፣ ተገቢ በሆነውና ማንምሰው በቀላሉ ሊገነዘበው የሚችለውን የህይወት አድን መስፈርት በትላልቅ የንግድ አገልግሎት ዘርፍ ለሚሰሩ ሰራተኞች መከልከሉ አሳዝኖኛል” ብለዋል፡፡

10 ሚሊዮን የሚሆኑ ሠራተኞች አሉበት በተባለው በጤናው ዘርፍ የተላለፈውን ውሳኔ ግን በደስታ የተቀበሉት መሆኑን ባይደን አስታውቀዋል፡፡

የፍሎሪዳው ሴናተር ሪክስካት “የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የፌዴራል ሥልጣናቸው ከገደብ በላይ እያለፈ ለመጣው ባይደን፣ ንጉሥ አለመሆናቸውን በመንገር ግልጽ መልዕክት አስተላልፎላቸዋል” በማለት አድንቀውታል፡፡

XS
SM
MD
LG