በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትረምፕ አስተዳደር በኮቪድ-19 ላይ


ፎቶ ፋይል፦ የብሄራዊ የአለርጂና የተላላፊ በሽታዎች ተቋም ዳይሬክተር ዶ/ር አንተኒ ፋውቺ
ፎቶ ፋይል፦ የብሄራዊ የአለርጂና የተላላፊ በሽታዎች ተቋም ዳይሬክተር ዶ/ር አንተኒ ፋውቺ

የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ የህዝብ ጤና ጥበቃ ባለሥልጣናት ዛሬ በተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው የትረምፕ አስተዳደር ለኮቪድ-19 ቀውሶች እየሰጠ ሥላለው ምላሽ የምስክርነት ቃላቸውን ይሰጣሉ።

በሃገሪቱ አንዳንዶቹ አካባቢዎች የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር እያሻቀበ ሆስፒታል የሚገቡትም ህመመተኞች ቁጥር ጨምሯል።

ዛሬ ለምክር ቤት አባላት ቃላቸውን ከሚሰጡት ባለሥልጣናት መካከል የብሄራዊ የአለርጂና የተላላፊ በሽታዎች ተቋም ዳይሬክተር ዶ/ር አንተኒ ፋውቺ የብሄራዊ የበሽታዎች ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር ሮበርት ሬድፊልድ፣ የምግብና የመድሃኒት አስተዳደር ኃላፊ ዶ/ር ስቴፈን ሃንና የህዝብ ጤና አገልግሎት ዋና ኃላፊ አድሚራል ብረት ግሮይር ይገኙባቸዋል።

XS
SM
MD
LG