ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታ መቆጣጠርና የመከላከል ማዕከል፣ ትናንት ባስታወቀው መሰረት የኮሮናቫይረስ አየር ላይ ለሰዓታት ያክል በመቆየት ሊዛመት እንደሚችል ገልጿል።
በዚሁ መመሪያም መሠረት ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ብዙም የአየር ዝውውር በሌለበት ክፍል ውስጥ ሲሆኑ ከስድስት ጫማ በራቁ ሰዎችም ላይ ቢሆን ቫይረሱን ሊያስተላልፉ እንደሚችል ማስረጃ ማግኘቱን አስታውቋል።
ኮሮናቫይረስ በዋነኝነት ሊዛመት የሚችለው በአየር በኩል ሊሆን እንደሚችል የአሜሪካ የሳይንስ ጠቢባን የፃፉት ግልፅ ደብዳቤ ትናንት “ሳይንስ” በተባለው የህክምና መጽሄት ላይ ወጥቷል።