በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩናይትድ ስቴትስ በ20 ዓመት ውስጥ ከፍተኛ የጥላቻ ወንጀሎች ተመዘገቡ


በዩናይትድ ስቴትስ ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ የጥላቻ ወንጀሎች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ ወደ ሆነ ደረጃ መድረሱን ኤፍቢአይ አስታወቀ፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፌደራሉ ምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ)፣ እኤአ በ2021 የተመዘገበው የጥላቻ ወንጀል ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ ከነበረው እጅግ ከፍተኛው መሆኑን የጥላቻ ወንጀሎችን አስመልክቶ በሚያወጣው ዓመታዊ ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡

በተጠቀሰው የ2021 ዓመት ታህሳስ ወር ውስጥ 7ሺ262 የጥላቻ ወንጀሎች መመዝገባቸውንም ኤፍቢአይ ገልጿል፡፡

ይሁን እንጂ መረጃው እንደ ኒዮርክ፣ ቺካጎ እና ካሊፎርኒያ የመሳሰሉ ትላልቅ የፖሊስ መምሪያዎችን ጨምሮ ወደ 4ሺ ከሚጠጉ የህግ አስከባሪ ተቋማት ያገኛቸውን መረጃዎች ያላከተተ መሆኑን ተመልክቷል፡፡

በአገሪቱ ከሚገኙ የፖሊስ ተቋማት ተጨማሪ መረጃዎች እንዳገኘ በአገሪቱ ያለውን የጥላቻ ወንጀሎች መጠን በትክክል እንደሚገልጽም ኤፍቢአይ አስታውቋል፡፡

እስካሁን ያሉ ተጨማሪ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ባለፈው ዓመት የነበረው የጥላቻ ወንጀል በቀደመው ዓመት ከነበረው በ11.6 በመቶ መጨመሩን አስታውቋል፡፡

በካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርስቲ ሳን በርናርዲኖ፣ የጥላቻና ጽንፈኝነት ጥናት ማዕከል ዳይሬክተር፣ ብሬን ሌቪን፣ በኤፍ ቢ አይ መግለጫ የተጠቀሰው አሃዝ በተጨማሪነት ከቀረበው ሪፖርት ጋር ልዩነት ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እኤአ በ2021 የተመዘገቡት 10ሺ530 የጥላቻ ክስስቶች አንድን የጥላቻ ዓይነት ብቻ ነጥለው የሚያመለክቱ መሆናቸውን ሌቪን ገልጸዋል፡፡

ቪኦኤ በተባለው ልዩነት ዙሪያ ተጨማሪ ማብራሪያዎችን ለማግኘት ኤፍቢአይን ያነጋገረ ቢሆንም እስካሁን ምላሽ አላገኘም፡፡

XS
SM
MD
LG