በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሄይቲ ፕሬዚዳንት ግድያ የተጠረጠሩ ፍሎሪዳ ውስጥ ተያዙ


የቀድሞው የሄይቲ ፕሬዚዳንት ዦቨነል ሞዪስ
የቀድሞው የሄይቲ ፕሬዚዳንት ዦቨነል ሞዪስ

በሄይቲ ፕሬዚዳንት ግድያ የጠረጠሩ አራት ሰዎችን ፍሎሪዳ ውስጥ ትናንት መያዟን አሜሪካ አስታውቃለች፡፡

በእአአ ሃምሌ 2021 በመኖሪያ ቤታቸው ሳሉ በአሰቃቂ ሁኔታ ከተገደሉት የቀድሞው የሄይቲ ፕሬዚዳንት ዦቨነል ሞዪስ ግድያ ጋር በተያያዘ በአሜሪካ የተያዙት ተጠርጣሪዎች ቁጥር ወደ 11 ከፍ ብሏል፡፡

አራቱ ተጠርጣዎች ትናንት ማለዳ እንደተያዙ በፍሎሪዳ የሚገኝ የፌዴራል ፍ/ቤት አስራ አንዱንም ተጠርጣሪዎች ከፕሬዚዳንቱ ሞት ጋር በተገናኘ በተለያዩ ወንጀሎች ከሷል፡፡

ፕሬዚዳንቱን ከሥልጣን ለማስወገድ በሚፈልጉ የሄይቲ ዜጎችና ትውልደ ሄይቲ በሆኑ አሜሪካኖች ቀጣሪነት በኮሎምቢያዊ ነፍሰ ገዳዮች ፕሬዚዳንት ዦቨነል ሞዪስ ከተገደሉ በኋላ አገሪቱ ወደማያባራ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ገብታ ትገኛለች፡፡

የሄይቲ ባለሥልጣናት በደርዘን የሚቆጠሩ ተጠርጣሪዎችን ቢይዙም በዳኞች ላይ በሚሰነዘር የግድያ ዛቻ ምክንያት የፍርድ ሂደቱ ተስተጓጉሏል፡፡

የግድያ ሴራው የተጠነሰሰው በአሜሪካ ምድር ላይ ነው በሚል የአገሪቱ ባለሥልጣናት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት እርምጃ በመውሰድ ላይ ይገኛሉ፡፡

ባለፈው ወር አራት አሜሪካዊ ዜግነት ያላቸውን ትውልደ ሄይቲ ተጠርጣሪዎች ሄይቲ አሳልፋ ሰጥታለች፡፡ ከእነዚህ አንዱ ጥምር ዜግነት ያለውና ፕሬዚዳንት ዦቨነል ሞዪስን ለመተካት ይሻ የነበረ ግለሰብ ይገኝበታል፣ ተብሏል፡፡

XS
SM
MD
LG