በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአሜሪካ የበጋው የመጀመሪያ ሳምንት በርካቶች በጅምላ ጥቃት ሕይወታቸውን አጡ

በአሜሪካ የበጋው የመጀመሪያው ሳምንት መጨረሻ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች በመሣሪያ በተፈጸመ የጅምላ ጥቃት ሕይወታቸውን አጥተዋል።
በአሜሪካ የበጋው የመጀመሪያው ሳምንት መጨረሻ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች በመሣሪያ በተፈጸመ የጅምላ ጥቃት ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በአሜሪካ የበጋው የመጀመሪያው ሳምንት መጨረሻ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች በመሣሪያ በተፈጸመ የጅምላ ጥቃት ሕይወታቸውን አጥተዋል።

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ በአላባማ ግዛት በተዘጋጀ ፌስታ፣ በኦሃዮ የመዝናኛ መንደር እንዲሁም በአርካንሶ አንድ የሸቀጥ መደብር በተከፈተ ተኩስ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል አልያም ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በአሜሪካ በበጋው ወቅት የመሣሪያ ጥቃቶች በብዛት ይስተዋላሉ።

ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተከታታይ የደረሱት የጅምላ መሣሪያ ጥቃቶች፣ የከተማ አስተዳዳሪዎችን ከሌሎች ግዛቶችና ከፌዴራል መንስግስት ዕርዳታ እንዲጠይቁ አስገድዷል።

ትላንት እሁድ በመንገመሪ፣ አላባማ ሰዎች በብዛት ለፌስታ በተሰባሰቡበት ዝግጅት ላይ ከፍተኛ ተኩስ ተከፍቶ ዘጠና ሰዎች ተጎድተዋል። መርማሪዎች 350 የሚሆኑ የጥይት ቀልሆችን አግኝተዋል።

በሚቺጋን የተሰረቀ መኪናን ይከተል የነበረ የፖሊስ ዓባል በተተኮሰበት ጥይት ሕይወቱን አጥቷል። በፊላዴልፊያ ደግሞ አራት ሰዎችን አሳፍሮ የነበረን መኪና ያስቆመ ፖሊስ ተኩስ ተከፍቶበት ክፉኛ ተጎድቷል ተብሏል።

በከለምበስ፣ ኦሃዮ በሚገኝ የመዝናኛ መንደር በተከፈተ ተኩስም 10 ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በአርካንሶ በምትገኝ አንዲት ትንሽ ከተማ፣ ሱቅ ውስጥ በተከፍተ ተኩስ አራት ሰዎች ሲሞቱ፣ 11 ተጎድተዋል። ከሟቾቹ ውስጥ ጥቃት አድራሹ እና የ23 ዓመት እመጫት ይገኙበታል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG