ዋሺንግተን ዲሲ —
የዋይት ሃውስ ቤተ መንግሥት ያረቀቀው ገና ያልተፈረመ ባለ ሰባት ገፅ የሥምምነት ዕቅድ ሃሳብን የአሜሪካ ድምፅ አግኝቷል።
በዩናይትድ ስቴትስና በጓቲማላ መካከል “የአስተማማኝ ሦስተኛ ሃገር” ፕሮቶኮል ይመሰርታል። ረቂቀ ሃሳቡ በያዝነው ሳምንት ለጓቲማላ መንግሥት ይቀርባል።