የፌዴራል መሥራያ ቤቶች በተዘጉበት ወቅት ያለ ክፍያ ለሠሩ የፌዴራል ሠራተኞች ደምወዛቸው እንደሚከፈላቸው ዋስትና የሚሰጠውን ህግ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ዛሬ እንደሚፈርሙ ተገለጸ።
ብዙዎች እንደሚሉት ግን፣ ፕሬዚዳንቱና ዴሞክራቶች ከመፍትሔው ብዙ ርቀት ላይ በመሆናቸው፣ በከፊል ከተዘጉ ዛሬ 26ኛ ቀናቸውን የያዙት መሥራያ ቤቶች መቼ እንደሚከፈቱ አለመታወቁ ነው።
ወደ 800,000 የሚሆኑ የፌዴራል መንግሥቱ ተቀጣሪዎች፣ ወይ ከሥራ ቀርተው ቤታቸው ናቸው አልያም ያለ ክፍያ እየሰሩ ናቸው።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ