በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ ም/ቤት በበጀት ላይ ስምምነት ሊደርስ ባለመቻሉ በሚቀጥለው ሳምንት የመንግስት ሥራ ሊቆም ይችላል


አፈ ጉባኤ ከቪን ማካርቲ 
አፈ ጉባኤ ከቪን ማካርቲ 

የአሜሪካ ሴኔት እና የተወካዮች ም/ቤት አባላት፤ በሀገሪቱ የበጀት መጠን፣ ለዩክሬን በሚሰጠው ድጋፍ፣ ከሜክሲኮ ጋር በሚያዋስነው ድንበር በኩል ስለሚገቡ ፍልሰተኞች እንዲሁም በድህነት ውስጥ ለሚኖሩ አሜሪካውያን የሚሰጠውን ድጋፍ በተመለከተ መስማማት ላይ ባለመድረሳቸው፣ የመንግስት ሥራ የመዘጋቱ ሁኔታ አይቀሬ መስሏል።

በዲሞክራቶች ቁጥጥር ሥር ያለው ሴኔት፣ መንግስትን ከመዘጋት ለመታደግ ለሰባት ሳምንት የሚቆይ ግዜያዊ በጀት ለማጽደቅ በመሞከር ላይ ቢሆንም፣ ም/ቤቱን የሚቆጣጠረው የሪፐብሊካን ፓርቲን የሚወክሉት አፈ ጉባኤ ከቪን ማካርቲ የሴኔቱን ሕግ ለም/ቤቱ ድምጽ እንደማያቀርቡ አስታውቀዋል።

ሴኔቱ እና ም/ቤቱ እስከ ቅዳሜ እኩለ ሌሊት ድረስ አንድ ስምምነት ላይ ካልደረሱ፣ ከእሁድ ጀምሮ በጀት ስለማይኖር፣ ”አስፈላጊ” ከተባሉ ሰራተኞች በስተቀር በጀት መልሶ እስከሚለቀቅ ድረስ የመንግስት ሠራተኞች ሥራ ያቆማሉ።

የመንግስት መ/ቤቶች ዛሬ ሐሙስ መንግስት ሊዘጋ እንደሚችል ለሠራተኞች አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG