የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ከባድ ዝናባማው አውሎ ነፋስ (ሄሪኬን ሚልተን) አስቀድሞ የታቀደው ጉዟቸውን ለአንድ ሳምንት ከአስተጓጎለው በኋላ ዛሬ ሐሙስ ወደ ጀርመን አቅንተዋል።
ባይደን እና የጀርመኑ መሪ፣ ሁለቱም በቅርቡ ለዩክሬን ይፋ ያደረጉት አዲስ የደህንነት እርዳታ እና የሚሰጡትን ድጋፍ አስመልክቶ ከፍተኛ ጫና እያጋጠማቸው ነው።
ዩክሬን በመሪዎቹ የመነጋገሪያ አጀንዳ በዋናነት ከተቀመጡት መካከል ናት፡፡
ዋይት ሀውስ ፕሬዚደንት ባይደን ሌላ የ425 ሚሊዮን ዶላር ጥቅል የደህንነት ድጋፍ ይፋ ማድረጋቸውን ትላንት ረቡዕ አስታውቋል።
መድረክ / ፎረም