በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“አሜሪካ ጋዛን በባለቤትነት መያዝ ትሻለች” ትረምፕ


ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ምኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋራ በመሆን ዋሽንግተን ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ
ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ምኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋራ በመሆን ዋሽንግተን ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ

ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ አሜሪካ ጋዛን በባለቤትነት መቆጣጠር እንደምትሻ አስታውቀዋል። ከዚህ ቀደም ፕሬዝደንቱ ጦርነት ባፈራረሳት ሰርጥ ውስጥ የሚኖሩ ፍልስጤማውያን ወደ ጎረቤት ጆርዳን እና ግብጽ ሄደው እንዲሰፍሩ ሐሳብ አቅርበው ነበር።

የፍልስጤም ራስ ገዝ፣ ግብጽ፣ ሳዑዲ አረቢያና ሌሎችም የአሜሪካ ሸሪኮችም ሆነ ወዳጅ ያልሆኑ ሃገራት የትረምፕን ሃሳብ ተቃውመዋል።

“ያነጋገርኳቸው ሰዎች በሙሉ አሜሪካ ጋዛን በባለቤትነት ትያዝ የሚለውን ሐሳብ ወደውታል። ድንቅ የሆነውን ሥፍራ በማልማትም በሺሕ የሚቆጠር የሥራ ዕድል ይፈጠራል” ብለዋል ትረምፕ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ምኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋራ በመሆን ዋሽንግተን ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ።

ኔታንያሁ በበኩላቸው ዋናው ግባቸው ሐማስ በእስራኤል ላይ ስጋት ማረጋገጥ ቢሆንም፣ “ትረምፕ ደግሞ ግቡን ከፍ አድርገውታል” ብለዋል።

“ታሪክን የሚቀይር ይመስለኛል፣ ይህን መንገድ መከተል ጠቃሚ ነው” ሲሉም ተደምጠዋል ኔታንያሁ።

በ15 ወራት ጦርነት የፈረሰውን ሥፍራ ለመቆጣጠር ያላቸውን ዕቅድ ዝርዝር ትረምፕ አላሳወቁም። የአሜሪካ ወታደሮችን መላክም ከአማራጮች ዝርዝር ውስጥ አለመውጣቱን ትረምፕ አስታውቀዋል። “አስፈላጊ ከሆነ እናደርገዋለን። ያንን ሥፍራ ይዘን እናለማዋለን” ብለዋል ትረምፕ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG