በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ ኀይሎች ቀይ ባሕር ላይ ስድስት የሁቲ ድሮኖችን ደመሰሱ

የዩናይትድ ስቴትስ ጦር፣ በቀይ ባሕር ላይ በኢራን በሚደገፉ የሁቲ ዐማፅያን የሚንቀሳቀሱ ስድስት ሰው አልባ አውሮፕላኖችን አወደመ።
የዩናይትድ ስቴትስ ጦር፣ በቀይ ባሕር ላይ በኢራን በሚደገፉ የሁቲ ዐማፅያን የሚንቀሳቀሱ ስድስት ሰው አልባ አውሮፕላኖችን አወደመ።

የዩናይትድ ስቴትስ ጦር፣ በቀይ ባሕር ላይ በኢራን በሚደገፉ የሁቲ ዐማፅያን የሚንቀሳቀሱ ስድስት ሰው አልባ አውሮፕላኖችን አወደመ።

ጥቃቱ የደረሰው፣ የሁቲ ዐማፅያን ሁለተኛው የንግድ መርከባቸው መስጠሙ በተረጋገጠበት ተመሳሳይ ቀን ነው፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ማዕከላዊ ዕዝ፣ ትላንት ኀሙስ በባሕሩ ላይ የነበሩ አራት ሰው አልባ መርከቦችንና ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ሁለት ድሮኖችን ማውደሙን አስታውቋል።

በጥቃቱ፣ በዩናይትድ ስቴትስ በኩል የተገለጸ ምንም ዐይነት ጉዳት ባይኖርም፣ ሰው አልባ አውሮፕላኖቹ ኹነኛ ስጋት ፈጥረው እንደነበር ተመልክቷል፡፡

እ.አ.አ ሰኔ 12 ቀን፣ በሁቲ ሚሳየል የተመታች የጭነት መርከብ መስጠሟ ሲነገር፣ በውስጧ የነበረ አንድ ሠራተኛ ተገድሏል፡፡

የአሜሪካ የመከላከያ መረጃ ተቋም ባወጣው ሪፖርት፣ ሁቲዎች፥ በዓለም አቀፍ መርከቦች ላይ የሚያደርሷቸው ጥቃቶች፣ በሉላዊው ንግድ እና የርዳታ አቅርቦት ላይ ተጽእኖ እያሳደሩ ነው፤ ብሏል።

በአካባቢው በአሜሪካ የሚመራው ወታደራዊ ዘመቻ፣ በየቀኑ ሊባል በሚችል መልኩ፣ በጦር እና በንግድ መርከቦች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች እንደሚያጋጥሙት ተገልጿል፡፡ ይህም፣ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ከፍተኛ የባሕር ላይ ውጊያ መኖሩን ያሳያል፤ ተብሏል፡፡

ሁቲዎች፣ በጋዛው ጦርነት ሐማስን ለመደገፍ፣ ካለፈው ኅዳር ወር ጀምሮ፣ በርካታ የሰው አልባ አውሮፕላኖችንና የሚሳዬል ጥቃቶችን፣ በቀይ ባሕር ላይ በሚንቀሳቀሱ መርከቦች ላይ እያካሔዱ ይገኛሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG