በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍሎሪዳ ውስጥ አነስተኛ አውሮፕላን ተከስክሶ ብዙ ሰው ሞተ


የእሳት አደጋ ሠራተኞች እና ሌሎች ባለሥልጣናት አደጋው የተከሰተበት ሥፍራ በሥራ ላይ ክሊርዋተር ከተማ ቤይሳይድ፣ ፍሎሪዳ እአአ የካቲት 1/2024
የእሳት አደጋ ሠራተኞች እና ሌሎች ባለሥልጣናት አደጋው የተከሰተበት ሥፍራ በሥራ ላይ ክሊርዋተር ከተማ ቤይሳይድ፣ ፍሎሪዳ እአአ የካቲት 1/2024

ትላንት ሐሙስ ምሽት ላይ በዩናይትድ ስቴትስ ፍሎሪዳ ግዛት ውስጥ አውሮፕላን ተከስክሶ፣ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩና አንድ የአካባቢውን ሰው ጨምሮ ብዙ ሰው መሞቱን ባለሥልጣናት ተናገሩ።

አውሮፕላኑ ክሊርዋተር ከተማ ቤይሳይድ በተባለ አካባቢ በሚገኝ አንድ ተንቀሳቃሽ ቤት ላይ በመውደቁ ከነዋሪዎቹ አንዱ ሕይወቱ አልፏል።

አደጋውን ተከትሎ የተነሳው እሳት በፍጥነት ቢጠፋም ቢያንስ ሌሎች ሦስት ቤቶች በተነሳው ቃጣሎ ጉዳት እንደደረሰባቸው፣ የክሊርዋተር የእሳት አደጋ መከላከያ ኃላፊ ስካት ኤህለርስ ስለ አደጋው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።

አደጋው ከመድረሱ አስቀድሞ የባለ አንድ ሞተሯ አውሮፕላን አብራሪ ድንገተኛ አደጋ እንዳጋጠመው ለሴንት ፒት ክሊርዋተር ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ማስታወቁን የዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር ገልጿል።

አውሮፕላን ማረፊያው ከክሊርዋተር ደቡብ ምስራቅ 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል። የፍሎሪዳ ባለሥልጣናት እና የፌደራል መርማሪዎች አደጋው የደረሰበትን ስፍራ እንደሚመረምሩ ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG