በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአሜሪካ ተስተጓጉሎ የነበረው የአገር ውስጥ በረራ እንደገና ቀጥሏል


መንገደኞች በረራ በመስተጓጎሉ በተርሚናል ሲተላለፉ ይታያል፣ ሮናልድ ሬገን ዋሽንግተን ብሔራዊ አውሮፕላን ማረፊያ በአርሊንግተን፣ ቨርጂኒያ።
መንገደኞች በረራ በመስተጓጎሉ በተርሚናል ሲተላለፉ ይታያል፣ ሮናልድ ሬገን ዋሽንግተን ብሔራዊ አውሮፕላን ማረፊያ በአርሊንግተን፣ ቨርጂኒያ።

የዩናይትድ ስቴትስ የፌዴራል አቪዬሽን አስተዳደር (ኤፍኤኤ) በኮምፒውተር ሥራዓቱ ላይ በተከሰተ የኃይል መቋረጥ ምክንያት የአገር ውስጥ በረራ እንዲቆም ዛሬ ማለዳ ያወጣው መመሪያ መቀየሩንና በረራዎች ቀስ በቀስ ወደ ወትሮው እየተመለሱ መሆኑን አስታውቋል።

አስተዳደሩ ዛሬ ማለዳ አየር መንገዶች የአገር ውስጥ በረራ እንዲያቆሙ አዞ የነበረ ሲሆን፣ ይህም በኮምፒውተር መገናኛ ሥራዓቱ ላይ ባጋጠመው እክል ምክንያት እንደነበርና እገዳው ግን መነሳቱን አስታውቋል።

የችግሩን መንስኤ ለማወቅ እየሠራ መሆኑን ኤፍኤኤ በትዊተር መልዕክቱ ገልጿል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የመገናኛ ሚኒስትራቸውን ፒት ቡተጂጅ እንዳናገሯቸውና ጉዳዩን በተመለከተ በቀጥታ ለእርሳቸው ሪፖርት እንዲያደርጉ እንዳዘዟቸው ለማወቅ ተችሏል።

የዋይት ሃውስ ፕሬስ ኃላፊ ካሪን ዣን-ፔር በበኩላቸው በትዊተር እንደጻፉት የሳይበር ጥቃት እንደሆነ የሚያመላክት ማስረጃ እንዳልተገኘና ፕሬዚዳንቱ የትራንስፖርት ሚኒስቴሩ የችግሩን መንስኤ በተመለከተ ሙሉ ምርመራ እንዲያደርግ አዘዋል።

ችግሩ መጀመሪያ የታወቀው ጠዋት 12 ሠዓት ላይ ሲሆን፣ አንድ ሰዓት ገደማ ላይ 1,200 የሚሆኑ በረራዎች እንዲዘገዩ መደረጉ ታውቋል።

XS
SM
MD
LG