በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፌስቡክ ስለ ጎጂ ጎኖቹ እንዲያስረዳ ተጠየቀ


ፌስቡክ ስለ ጎጂ ጎኖቹ እንዲያስረዳ ተጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:30 0:00

ፌስቡክ ስለ ጎጂ ጎኖቹ እንዲያስረዳ ተጠየቀ

ፌስ ቡክ እንደገና ተመልሶ አነጋጋሪ ድርጅት ሆኗል፡፡ የዎል ስትሪት ጆርናል በቅርቡ ያወጣው ሪፖርት በድርጅቱ ውስጥ የሚታወቀው የፌስቡክ ጎጂ ተጽእኖ የውስጥ አለመገባባት መፍጠሩን አሳይቷል፡፡ የድርጅቱን የውስጥ አሰራር ያጋለጡት የቀድሞ የፌስቡክ ሠራተኛ በዚህ ሳምንት አደባባይ በመውጣት በማህበረባዊ የትስስር ሚዲያው ድርጅት ላይ መመስከራቸው ድርጅቱ ላይ ለሚካሄደው ምርመራ ተጨማሪ ሆኗል፡፡

ግዙፉ የማህበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ኢንስታግራም እና ዋትስ አፕ የተሰኙ ተጨማሪ የማህበራዊ ሚዲያ የትስስር መድረኮችን ይቆጣጠራል፡፡

ድርጅቱ አሁን ተመልሶ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

የቀድሞ የፌስቡክ ሠራተኛ ፍራንስስ ኻውገን እንዲህ ብለዋል

ዛሬ እዚህ ያለሁት ምክንያት የፌስቡክ ውጤቶችን ህጻናትን ስለሚጎዱ፣ ክፍፍልን ስለሚፈጥሩና ዴሞክራሲያችንን ስለሚያዳክሙ ነው፡፡

ፍራንስስ ኻውገን፣ ፌስቡክ ውስጥ፣ የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ሆነው ሆነው ለሁለት ዓመት ሠርተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ከዚያ ወዲህ፣ የድርጅቱን አሰራር በማጋለጥ ይታወቃሉ፡፡

ትናንት ማክሰኞ ኻውገን በህግ መወሰኛው ምክር ቤት ፊት ቀርበው ፣ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡ በድርጅቱና ከድርጅቱ ጋር ተያይዘው ባሉ እንደ ኢንስታግራም አይነቶቹን አፕልኬሽኖች አስመልከቶ ባሉ ችግሮች ላይ፣ ሆን ብሎ እርምጃ ያለመውሰድ ዳተኝነትና ግልጽነት የጎደለው አሰራር መኖሩም መስክረዋል፡፡

መስካሪዋ ፌስቡክ በአሰራሩ ከእውነት ይልቅ በአብዛኛው የቅጥፈት ወሬዎችን በፍጥነት በማሰራጨትና፣ የተሳሳቱ የኢንፎርሜሽን ዘመቻዎችን በዩናይትድ ስቴትስም ሆነ በመላው ዓለም ወደ መርጨት ያደላል ብለዋል፡፡

ፍራንሰስ ኻውገን እንዲህ ይላሉ

“የድርጅቱ አመራሮች ፌስብኩና ኢንስተግራምን እንዴት አደርገው ደህንነቱ የተጠበቀ መድረክ ማድረግ እንደሚቻል ያውቃሉ፡፡ ይሁን እንጂ በከፍተኛ መጠን የሚያጋብሱት ትርፍ በመኖሩ ሰዎችን የሚያስቀድም ለውጥ ማድረግ አይፈልጉም፡፡”

ፌስቡክ ራሱ እንዳደረገው ጥናት ኢንስታግራምን የሚጠቀሙ 32 ከመቶ የሚሆኑን ወጣት ልጃገረዶች ስለ ሰውነት ቅርጻቸው መጥፎ ስሜት እንደሚሰማቸው የገለጹ ሲሆን ኢንስተግራም የበለጠ ያባባሰባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ፍራንሰስ ኻውገን እንዲህ ይላሉ

“ፌስቡክ በፈጠረው የማጉያ ቀመሮቹ (amplification algorithms) የተጠቃሚዎችን ደረጃ ለመመድብ አጎልቶ የሚያጋንኑ መስፈርቶችን ይጠቀማል፡፡ ይህ ህጻናትን እንደ ጤናማ የምግብ አሰራሮች ከሚመስሉ ገራገር ጉዳዮች አንስቶ...የአመጋገብ ጉድለትን እስከሚሰብኩ ይዘቶች ድረስ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲተዋወቁ ያደርጋል፡፡”

ፌስቡክ ግን ኻውገን በምስክርነታቸው ወቅት የተናገሩት በድርጅቱ ውስጥ መመልከት ከቻሉት ከተወሰኑት የጥናትና የፖሊሲ ውጤቶች ብቻ ተነስተው ይላል፡፡

የኒው ሜክስኮ ክፍለ ግዛት ዴሞክራቱ ሴነተር ቤን ሬ ሉጃን ፣ የሚከተለውን ጥያቄ ለፌስ ቡክ የዓለም አቀፍ ደህንነት ኃላፊ አንቲገን ዴቪስሰንዝረዋል፡፡

“ፌስቡክ በተጠቃሚዎች ላይ ጎዳት ሊያመጣ የሚችል ለውጥ በመድረኩ ላይ ተመልክቶ ያውቃል? በተጠቃሚዎች ቁጥርም ሆነ በገቢ ላይ ጭማሪ ሰለሚያመጣስ ወደፊት ገፍቶበታል?”

የፌስ ቡክ ዓለም አቀፍ ደህንነት ኃላፊው አንቲገን ዴቪስ እንዲህ በማለት መልሰዋል

“እንደዚያ ያለ ነገር በበፍጹም በፌስቡክ ተሞክሮ ተከስቶ አያውቅም፡፡መድረካችንን ለሚጠቀሙ ሰዎች ደህንነት በሚገባ እንጨነቃለን፡፡ለዚህም 12 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨርስትመት አድርገንበታል፡፡ በዚህ ላይ የሚሰሩ በሺዎችና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች አሉን፡፡ ጉዳዩን የምናስተናግደው በዚያ መንገድ ነው፡፡”

“በኢንተርኔት በሴቶች ላይ የምታደርሱትን ጥቃት አቁሙ” የሚል ድርጅት መስራችና የፌስ ቡክ ተቺ የሆኑት፣ ሸሪን ሚሸል የፌስ ቡክ ሰዎች ሁሌም ቃላቸው እንዲሰጡ ሲጠየቁ ፣በሚሰጧቸው መልሶች

“ወደፊት እናሻሽላለን፣ የተለየን የተሻልንን እንሆናለን” ይላሉ፡፡ ከዚያ በቃ ይሄዳሉ ምንም የሚፈጠር የለም፡፡ ወይም በአብዛኛው ምንም የተፈጠረ ነገር የለም፡፡” ብለዋል፡፡

አያይዘውም እንደሚመስለኝ ግን ለመጀመሪያ ጊዜ አሁን ማረጋገጫ የተገኘ ይመስለኛል፡፡ መረጃው እያላቸው፣ ማድረግ ያለባቸው ነገር መኖሩን እያወቁ ግን ያላደረጉት ነገር ነው፡፡ በቃ አላደረጉትም፡፡” ብለዋል፡፡

አንዳንዶቹ ፌስቡክን ትንባሆ ድርጅቶችን ገጥሟቸው ከነበረው አስጨናቂ ጊዜ ጋር ያመሳስሉታል፡፡

ዴሞክራቱ ሴነተር ሪቻርድ ብሉሜንታል እንዲህ ይላሉ

“ፌስቡክ እና ትላልቆቹ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች ትልቁ የትንባሆው ዘመን የገጠማቸው ይመስላል፡፡ ሂሳብ የሚያወራርዱበት ጊዜ፣ ትላልቆቹ የትንባሆ ድርጅቶቹ ምርታቸው ካንሰር እንደሚያመጣ ማወቃቸው ብቻ አይደለም፡፡ ራሳቸው ሰርተው የደረሱቧቸውን ጥናቶችን መኖሩን ስናውቅ ፋይሎቹን ሰውረዋቸዋል፡፡”

ፌስ ቡክ ጉዳት ማምጣቱን አስመልክቶ በቀረበው ክስ፣ ህግ አውጭዎችና ተቆጣጣሪ ተቋማት ውሳኔዎችን መውሰድ አለመውሰዳቸው ፣ የሚታይ ይሆናል፡፡ ፌስቡክም የሚሰጠው ምላሽ ምን ሊሆን እንደሚችል ግልጽ አልሆነም፡፡

XS
SM
MD
LG