በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እሥረኛው በሞት ተቀጣ


ዩናይትድ ስቴትስ በ17 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ እሥረኛን በሞት ቀጣች። የሃገሪቱ ጠቅላይ ፍ/ቤት፣ አንድ የታችኛው ፍርድ ቤት ትዕዛዝን 5በ4 ድምፅ ዛሬ ከሻረ በኋላ ነው፣ የሞት ቅጣቱ የተፈፀመው።

የታችኛው ፍ/ቤት፣ በያዝናው ሳምንት እንዲፈፀሙ ታቅደው የነበሩት፣ ሦስት የሞት ቅጣቶችና ለመጭው ሳምንት፣ ቀጠሮ የተያዘላቸው የሞት ቅጣቶች እንዲዘገዩ ነበር ያዘዘው።

በሞት የመቅጣቱ ዘዴ፣ ሰዎች ጭካኔ በተመላበት ሁኔታ እንዳይቀጡ የሚያዘውን፣ የህገ-መንግሥት አንቅጽ ይጥስ እንደሆን ለማየት፣ ፍርድ ቤቶች በቂ ጊዜ እንዲኖራቸው በሚል ነበር፣ አንድ የፌዴራል ፍርድ ቤት ያዘገየው።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዛሬ ይህን ውሳኔ ከሻረ በኋላ፣ ዛሬ በሞት የተቀጣው እስረኛ ዳንኤል ለዊስ ሊ የተባለ ሲሆን፣ እአአ በ1996 የ8 ዓመት ዕድሜ ልጅ የምትገኝበት፣ ሦስት አባላት ያሉት ቤተሰብን በመግደል የተፈረደበት ሰው ነበር።

XS
SM
MD
LG