በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለጋሾች ለየመን ብድር ለመስጠት ቃል ገቡ


ፎቶ ፋይል፦ የተፋናቃዮች መንደር ማሪብ የመን
ፎቶ ፋይል፦ የተፋናቃዮች መንደር ማሪብ የመን

በዩናይትድ ስቴትስ እና በአውሮፓ ሕብረት የተመሩ ለጋሾች 600 ሚሊየን ዶላር ለየመን ብድር ለመስጠት ቃል ገቡ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም የመን ያለባት የገንዘብ ችግር ሚሊዮኖችን ለርሃብ እንደሚዳርግ አሳስቡዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ 290 ሚሊየን ዶላር ተጨማሪ ድጋፍ ቃል ገብታለች። ይህ የተመድ ዓለም አቀፍ አስከፊ የሰብዓዊ ሁኔታ ሲል የጠራው ጦርነት ግን መቆም እንዳለበት አሳስባለች፡፡

“የስብዓዊ እርዳታ በሰዎች ሕይወት ላይ መሰረታዊ የሆነ ለውጥ ያመጣል ነገር ግን ብቻውን ቀውሱን አይፈታውም” ሲሉ የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስተር አንተኒ ብሊንከን በተመድ የገንዘብ ርዳታውን ቃል በገቡበት ንግግራቸው አስገንዝበዋል፡፡

የመንን እጅግ የጎዳትን የዓየር ድብደባ ያካሄደችው ሳዑዲ አረቢያና የሁቲ አማጺን እንዲሁም መንግሥት በሃገሪቱ ውስጥ ምጣኔ ሃብቱ እንዲደቅ በማድረግ የመናዊያንን የጎዳውን እና የተቋረጠውን የነዳጅ መስመር እንዲቀጥል መንገድ እንዲፈልጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG