በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓ ህብረት የንግድ ስምምነት

ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን
ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን

ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓ ህብረት ለረጅም ዓመታት ባነታረካቸው ከባድ ንግድ ነክ ጉዳይ ስምምነት ማድረጋቸው ተገለጠ።

ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓ ህብረት ለአውሮፕላን አምራቹ ኤርበስ ኩባኒያ በሚሰጡ ድጎማዎች ጉዳይ ለረጅም ጊዜ የዘለቀውን ሙግታቸውን የሚቋጭ ስምምነት ማድረጋቸው ተዘግቧል።

በዚህም መሰረት ዩናይትድ ስቴትስ የአውሮፕላን አምራች ኩባኒያዋ ዋና ተፎካካሪ የሆነው ግዙፉ ኤርበስ ኩባኒያ ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ ድጎማዎች የሚያገኝ በመሆኑ በዓለም የንግድ ድርጅት ፈቃድ የጣለችውን ታሪፍ ለአምስት ዓመታት ከቅድመ ሁኔታ ጋር አቆራኝታ ልታቋርጥ ተስማምታለች።

የአውሮፓ ኮምሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሊየን ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጋር ዛሬ መደበኛ ንግግር መክፈቻ ላይ በሰጡት ቃል

"ጉባኤዋችን አውሮፕላኖችን በሚመለከት ስምምነት ተጀምሯል" ብለዋል። አስከትለውም "ይህ ከአስራ ሰባት ዓመታት ንትርክ በኋላ አውሮፕላኖችን የሚመለከቱትን ጉዳዮች በሙግት ሳይሆን በትብብር ለመፍታት ወደሚያስችለን አቅጣጫ የሚወስደንን የግንኙነቶቻችን አዲስ ምዕራፍ መከፈት የሚያበስር ነው" ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የንግድ ተወካይ ካትሪን ታይ በበኩላቸው ስምምነቱ የዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓን ግንኙነት ለረጅም ጊዜ አጎምዝዞት የቆየውን የንግድ ጭቅጭቅ ይፈታል" ብለዋል። ከታላላቅ አጋሮቻችን ጋር ከመታገል ይልቅ አብረን ሆነን፣ ቻይና በንግድ ዘርፍ ከገበያ ውጭ የምትፈጽመውን ተግባር የፍትሃዊ ፉክክር መርሃችንን በሚያንጸባርቅ መንገድ ልንጋፈጥ እና ልንገዳደራት ተስማምተናል" ሲሉ አስረድተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአውሮፓ መሪዎች ዩናይትድ ስቴትስ ከአውሮፓ ጋር ያላትን ግንኙነት ከቀደሙት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በተለየ መንገድ እየመሩ ላሉት ለፕሬዚደንት ጆ ባይደን የሞቀ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ትረምፕ በአራቱ ዓመት የሥልጣን ዘመናቸው የአውሮፓ ሃገሮችን በወይን ጠጅ እና በአይብ ላይ ሳይቀር ቀረጥ ሲያስከፍሉዋቸው እንዲሁም የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት/ኔቶ/ የጋራ መከላከያ የሚገባችሁን መዋጮ የማትከፍሉ በማለት በቁጣ ሲነቅፉዋቸው እንደነበር ይታወሳል።

ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ከአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ቮን ሌየን እና ከአውሮፓ ህብረት ፕሬዚደንት ሻርል ሚሼል ጋር ሆነው በብረሰልሱ የህብረቱ ጽህፈት ቤት የመታሰቢያ ፎቶ በተነሱበት ሥነ ስርዓት ላይ በሰጡት ቃል "የእኔ አመለካከት ከቀደሙት ፕሬዚዳንት በጣም የተለየ ነው፡ ብለዋል።

የአውሮፓ ህብረቱ መሪ ሚሼልም "አሜሪካ ወደዓለም መድረክ ተመልሳለች" ብለዋል።

ይሄ ለአጋሮቻችን ብቻ ሳይሆን ለመላው ዓለም ታላቅ ዜና ነው ያልይ ኡርሱላ ቮን ዴር ሊየን በበኩላቸው "በስልጣን ዘመንዎ መጀመሪያ ሰሞን መምጣትዎ ራሱ ለአውሮፓ ህብረት በግልዎ ያለዎትን ቀረቤታ የሚያንጸባርቅ ነው፥ እናመስግንዎታለን ፥ ያለፈው አራት ዓመት ቀላል አልነበረም " ብለዋቸዋል።ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓ ህብረት ለረጅም ዓመታት ባነታረካቸው ከባድ ንግድ ነክ ጉዳይ ስምምነት ማደርጋቸው ተገለጠ።

ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓ ህብረት ለአውሮፕላን አምራቹ ኤርበስ ኩባኒያ በሚሰጡ ድጎማዎች ጉዳይ ለረጅም ጊዜ የዘለቀውን ሙግታቸውን የሚቋጭ ስምምነት ማድረጋቸው ተዘግቧል።

በዚህም መሰረት ዩናይትድ ስቴትስ የአውሮፕላን አምራች ኩባኒያዋ ዋና ተፎካካሪ የሆነው ግዙፉ ኤርበስ ኩባኒያ ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ ድጎማዎች የሚያገኝ በመሆኑ በዓለም የንግድ ድርጅት ፈቃድ የጣለችውን ታሪፍ ለአምስት ዓመታት ከቅድመ ሁኔታ ጋር አቆራኝታ ልታቋርጥ ተስማምታለች።

የአውሮፓ ኮምሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሊየን ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጋር ዛሬ መደበኛ ንግግር መክፈቻ ላይ በሰጡት ቃል

"ጉባኤዋችን አውሮፕላኖችን በሚመለከት ስምምነት ተጀምሯል" ብለዋል። አስከትለውም "ይህ ከአስራ ሰባት ዓመታት ንትርክ በኋላ አውሮፕላኖችን የሚመለከቱትን ጉዳዮች በሙግት ሳይሆን በትብብር ለመፍታት ወደሚያስችለን አቅጣጫ የሚወስደንን የግንኙነቶቻችን አዲስ ምዕራፍ መከፈት የሚያበስር ነው" ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የንግድ ተወካይ ካትሪን ታይ በበኩላቸው ስምምነቱ የዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓን ግንኙነት ለረጅም ጊዜ አጎምዝዞት የቆየውን የንግድ ጭቅጭቅ ይፈታል" ብለዋል። ከታላላቅ አጋሮቻችን ጋር ከመታገል ይልቅ አብረን ሆነን፣ ቻይና በንግድ ዘርፍ ከገበያ ውጭ የምትፈጽመውን ተግባር የፍትሃዊ ፉክክር መርሃችንን በሚያንጸባርቅ መንገድ ልንጋፈጥ እና ልንገዳደራት ተስማምተናል" ሲሉ አስረድተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአውሮፓ መሪዎች ዩናይትድ ስቴትስ ከአውሮፓ ጋር ያላትን ግንኙነት ከቀደሙት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በተለየ መንገድ እየመሩ ላሉት ለፕሬዚደንት ጆ ባይደን የሞቀ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ትረምፕ በአራቱ ዓመት የሥልጣን ዘመናቸው የአውሮፓ ሃገሮችን በወይን ጠጅ እና በአይብ ላይ ሳይቀር ቀረጥ ሲያስከፍሉዋቸው እንዲሁም የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት/ኔቶ/ የጋራ መከላከያ የሚገባችሁን መዋጮ የማትከፍሉ በማለት በቁጣ ሲነቅፉዋቸው እንደነበር ይታወሳል።

ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ከአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ቮን ሌየን እና ከአውሮፓ ህብረት ፕሬዚደንት ሻርል ሚሼል ጋር ሆነው በብረሰልሱ የህብረቱ ጽህፈት ቤት የመታሰቢያ ፎቶ በተነሱበት ሥነ ስርዓት ላይ በሰጡት ቃል "የእኔ አመለካከት ከቀደሙት ፕሬዚዳንት በጣም የተለየ ነው፡ ብለዋል።

የአውሮፓ ህብረቱ መሪ ሚሼልም "አሜሪካ ወደዓለም መድረክ ተመልሳለች" ብለዋል።

ይሄ ለአጋሮቻችን ብቻ ሳይሆን ለመላው ዓለም ታላቅ ዜና ነው ያልይ ኡርሱላ ቮን ዴር ሊየን በበኩላቸው "በስልጣን ዘመንዎ መጀመሪያ ሰሞን መምጣትዎ ራሱ ለአውሮፓ ህብረት በግልዎ ያለዎትን ቀረቤታ የሚያንጸባርቅ ነው፥ እናመስግንዎታለን ፥ ያለፈው አራት ዓመት ቀላል አልነበረም " ብለዋቸዋል።

XS
SM
MD
LG